የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን በስሩ ያሉትን ለተለያዩ ፓርኮች ሙሉ ለሙሉ ለሶስተኛ ወገን በማስተላለፍ እንዲተዳደር ለማከራየት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በኪራይ ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር 73/2017
የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን በስሩ ያሉትን ለተለያዩ ፓርኮች ማለትም
- ሎት 1:- የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳዳር ኮርፖሬሽ በውስጡ የሚያስተዳድራቸው በኮሪደር ልማት የለሙ በካሳንችስ ፤ ሳር ቤት ፣ ለቡ ፣ ጀሞ ፣ መካኒሳ ፣ ጀርመን አደባባይ ፣ 4 ኪሎ ፣ 5 ኪሎ፣ ስድስት ኪሎ ፣ 24 ቀበሌ አካባቢ ፣ 22 አካባቢ ፣ መገናኛ ፣ ለም ሆቴል አካባቢ ፣ ለሚኩራ ፣ ሰሚት ፣ አቦ ማዞሪያ ፣ ቄራ ፣ ጎሮ ፣ ሂልተን አካባቢ፣ ብስራተ ገብኤል ፣ አንበሳ ጋራጅ ፣ ገርጂ መብራት ሀይል፣ ሽሮ ሜዳ ፣ አካባቢ የሚገኙ የተለያዩ ፓርኮችን ለማከራየት
- ሎት 2:- ኮልፌ ፓርክ ውስጥ የሚገኙ ሱቅና አዳራሽ፣ አቃቂ ፓርክ ውስጥ የሚገኙ ካፌና አዳራሽ፣በከንቲባ ቢትወደድ ፓርክ ውስጥ የሚገኙ ካፌና ሱቆችን ፣ አምባሳደር ፓርክ ውስጥ የሚገኙ ካፌዎችን እንዲሁም ሸገር ፓርክ ውስጥ የሚገኙ ሱቆችን ለማከራየት
- ሎት 3:- በፈረንሳይ ፓርክን የችግኝ ጣቢያውን ሳይጨምር ሙሉ ለሙሉ ለሶስተኛ ወገን በማስተላለፍ እንዲተዳደር ለማከራየት
- ሎት 4፡- ገዳመ እየሱስ ፓርክን ሙሉ ለሙሉ ለሶስተኛ ወገን በማስተላለፍ እንዲተዳደር ለማከራየት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በኪራይ ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የተጠቀሱትን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራጮች ተጋብዘዋል፡፡
- ተጫራቾች በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ አለበት ፡፡
- ፓርኮቹ ውስጥ ገብቶ ለመስራት ፍቃደኛ የሆነና ከተቋማችን ጋር ውል ገብቶ በገበያ ጥናት እና የመነሻ ዋጋ መሰረት ተወዳድረው አስፈላጊውን ክፍያ የሚከፍልና በውሉ መሰረት ግዴታውን መወጣት የሚችል፡፡
- የሚሰጠውን አገልግሎት የሚገልጽ አጭር እና ግልጽ ፕሮፖዛል ማቅረብ አለበት፡፡
- በግቢ ያሉ ፋውንቴኖችንና ፣ መናፈሻዎችን ፣ የመጸዳጃ ቤቶችን ፣ የጽዳት ፣ የጥበቃ ፣ የተለያዩ ጥገናዎችን ከሌሎች ተከራዮች ጋር በመሆኑን ማስጠገን ፣ መቆጣጠርና በአግባቡ ማስተዳደር የሚችል፡፡
- ለህዝብ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ተመጣጣኝ የገበያ ዋጋ ለማቅረብ ፍቃደኛ የሆነ፡፡
- ኮርፖሬሽኑና የከተማ አስተዳደሩ በሚያወጣው የስራ ሰዓት ቅዳሜ እና እሁድ ፣ በአላትን እንዲሁም ምሽትን ጨምሮ አገልግሎት መስጠት የሚችል፡፡
- አሸናፊነት ከታወቀ በኋላና ውል ከወሰደ በኋላ በ3 ቀን ውስጥ ስራ መጀመር የሚችል፡፡
- ስታንዳርዱን የጠበቀ እና የኮሊደር ልማቱን የሚመጥን እቃዎችን ይዞ መግባት የሚችል፡፡
- ከተቻለ በሬስቶራንት ፣ በካፌ እና ህዝብ መዝናኛ ፓርክ ላይ ልምድ ያለውና መረጃ ማቅረብ የሚችል።
- ተጫራቾች ለሎት አንድ እና ሁለት 50,000.00 (ሃምሳ ሺ ብር) ሎት 3 እና 4 100,000.00 (አንድ መቶ ሺ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲፒኦ ወይም ባንክ ጋራንቲ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን ስም ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 500 /አምስት መቶ ብር/ ቦሌ ማተሚያ ፊት ለፊት ገባ ብሎ የድሮው ፒኮክ መናፈሻ ግቢ ውስጥ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አስር ተከታታይ የስራ ቀን ከጠዋት 2፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ በመቅረብ መግዛት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ፋይናንሻል ዶክመንት እና ቴክኒካል ዶክመንት ለየብቻ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሳጥኑ እስከሚታሸግበት ከ10ኛው ተከታታይ የስራ ቀን በኋላ ባለው 11ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ድረስ ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ሳጥኑ ታሽጎ በዚያው ቀን ጠዋት 4፡30 ቦሌ ማተሚያ ፊት ለፊት ገባ ብሎ የድሮው ፒኮክ መናፈሻ ግቢ በግዥና ንብረት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- የጨረታ መክፈቻው ቀን ቅዳሜና እሁድ ላይ የሚውል ከሆነ በቀጣዩ ሰኞ በተጠቀሰው ሰዓት ተዘግቶ የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ዘግይቶ የደረሰ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ኮርፖሬሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ-ስልክ ቁጥር 0703614456 /0977246014 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሕዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን
