የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ምዕራብ ሪጅን የአሶሳ እና ግ/በለስ ቅ/ጽ/ቤት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል ቤት/ህንፃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለ5 (አምስት) ዓመት ለመከራየት ይፈልጋል።
በድጋሚ የወጣ የቢሮ ኪራይ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ምዕራብ ሪጅን የአሶሳ እና ግ/በለስ ቅ/ጽ/ቤት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል ቤት/ህንፃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለ5 (አምስት) ዓመት ለመከራየት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት ተወዳዳሪዎች፡-
- የቤት ይዞታ ማረጋገጫ ካርታ /ፕላን/ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
- ግብር የተከፈለበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
- የኔትዎርክ ዝርጋታ ለማሰራት የቤቱ ባለቤት ፈቃደኛ የሆነ
- የስራ ክፍሎች ብዛት የሚገልጽ በእስፔስፊኬሽን ውስጥ የተካተተ ይሆናል፡፡
- የቤቱ መገኛ ቦታ /Location/ ቢያንስ ኮብል መንገድ ዳር የሚገኝ፤
- የቤቱ/ህንፃው ለአረጋውያንና ለአካል ጉዳተኞች ለመገልገል ሲመጡ የመግቢያ ደጁ አመቺ የሆነ አቀማመጥ ያለው
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የተዘጋጀውን እስፔስፊኬሽን /ሰነድ/ ለአሶሳ ከተማ ከአሶሳ ቅ/ጽ/ቤት ለግ/በለስ ከተማ ከግ/በለስ ቅ/ጽ/ቤት በነፃ በመውሰድ ሞልቶው እስከ 15ኛዉ ቀን 10፡30 ሰዓት ድረስ በፖስታ አሽገው ማቅረብ የሚጠበቅባቸው ሲሆን ጨረታው የሚከፈተው በነቀምቴ ከተማ በሚገኘው ምዕራብ ሪጅን ጽ/ቤት ስለሆነ አስፈላጊውን ማስረጃ አሟልተው እንዲያስገቡ፡፡
- አሸናፊው ሲለይ ተወዳዳሪዎች ውሉን በቅ/ጽ/ቤቱ የሚዋዋሉ ይሆናል፡፡
ማሳሰቢያ ፡ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ
- ምዕራብ ሪጅን ጽ/ቤት ስልክ ቁጥር 057-661-5178
- አሶሳ ቅ/ጽ/ቤት ስልክ ቁጥር 057-775-0249
- ግ/በለስ ቅ/ጽ/ቤት ስልክ ቁጥር 058190439 ደውሎ መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ምዕራብ ሪጅን
