የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
|
ተ.ቁ |
የዕቃው አይነት |
መለኪያ |
የጨረታ ማስከበሪያ በብር |
|
1 |
አገልግሎት ላይ የዋሉ የተለያዩ የእንጨት ፓለቶች እና ቁርጥራጭ እንጨቶች |
በኪሎ |
300,000.00 |
|
2 |
አገልግሎት ላይ የዋሉ የአውሮፐላን እና የተሽከርካሪ ጎማዎች |
በኪሎ |
200,000.00 |
|
3 |
አገልግሎት ላይ የዋሉ የተለያዩ ቁርጥራጭ ብረቶች /Scrap steel, Stainless steel & cast Iran |
በኪሎ |
300,000.00 |
|
4 |
አገልግሎት ላይ የዋሉ የኩሽና ማሽኖች (Kitchen Machines) |
|
|
|
4.1 |
አገልግሎት ላይ የዋለ ፓን /Old Tilting Pans |
በቁጥር |
100,000.00 |
|
4.2 |
አገልግሎት ላይ የዋለ ቦይለር /Old Titing Boiler |
በቁጥር |
100,000.00 |
|
4.3 |
የውሃ ዶዘር /ማቀዝቀዣ ማሽን/ Water Doser/ Chiller Machine |
በቁጥር |
100,000.00 |
|
5 |
አገልግሎት ላይ የዋሉ የላውንደሪ ማሽኖች |
|
|
|
5.1 |
ጥቅም ላይ የዋለ ደረቅ ማጽጃ /USED DRY CLEANING/ |
በቁጥር |
200,000.00 |
|
5.2 |
ጥቅም ላይ የዋለ ማጠቢያ ማሽን /USED SUPREMA WET WASHER |
በቁጥር |
200,000.00 |
|
6 |
አገልግሎት ላይ የዋሉ የቢሮ ፈርኒቸሮች /Different used furniture |
በጥቀል |
200,000.00 |
|
7 |
የወረቀት መቆራረጫ ማሽን /USED PAPER SHREDDER |
በቁጥር |
15,000.00 |
ማሳሰቢያ፡-
ሀ) በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ለመግዛት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ ብር 600.00 (ስድስት መቶ ብር) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277 ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር WIMNA/C&SAT003/2017 በሚል ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡
ለ) በማናቸውም ግዜ የጨረታ ሰነድ የዋጋ መግለጫ ላይ የሚገለፀው ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስ ፤ የታክስ እና ሌሎች ማናቸውንም አይነት አስፈላጊ ክፍያዎችን አያካትትም፤ ማናቸውንም የቫት፤ የታክስ እና ሌሎች አስፈላጊ ክፍያዎችን በሙሉ የጨረታው አሸናፊ ይከፍላል፤
ሐ) ተጫራቾች የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ኦሪጅናል (Deposit slip) በመያዝ የጨረታ ሠነዱን ሰኔ 26 ቀን 2017 ዓ/ም እና ሰኔ 27 ቀን 2017 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 እንዲሁም ከሰዓት 07:00 እስከ 10:00 ቦሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የዋና መስሪያ ቤት መግቢያ በር ድረስ በመምጣት መግዛት ይችላሉ፡፡
መ) ተጫራቾች የዕቃዎቹን ናሙና ሐምሌ 01 ቀን 2017 ዓ/ም ከጠዋቱ 4፡00 እስከ 6፡00 እንዲሁም ከሰዓት 08:00 እስከ 10:00 ባለው ግዜ በድርጅቱ ቅጥር ግቢ በቡልቡላ በር በኩል በአካል በመገኘት መመልከት መጎብኘት ይችላሉ።
ሠ) ተጫራቾች ከላይ በሰንጠረዡ ላይ ለእያንዳንዱ የዕቃ/ዎች አይነት የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ /BID BOND/ በባንከ የገንዘብ ክፍያ ማዘዣ (C.P.O) ብቻ በቅድሚያ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፡፡ ለጨረታው ማስከበሪያ በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አይቻልም፡፡
ረ) ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሐምሌ 03 ቀን 2017 ዓ/ም ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት ላይ ቦሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የዋና መስሪያ ቤት ስብሰባ አዳራሽ ይሆናል፡፡ የጨረታው አሸናፊም በዚሁ ሰዓት ተጫራቾች ባሉበት ወዲያውኑ ተለይቶ ይታወቃል፡፡
ተጫራቾች በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡00 እስከ 4፡30 ሠነዳቸውን በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ለሚወዳደሩበት የዕቃ ዓይነት የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ (BID BOND) የሚገዙበትን ዋጋ ከሞላበት የጨረታ ሰነድ ጋር አብሮ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
ሰ) በትክክል የማይነበብ ፣ያልታሸገ ፖስታ እንዲሁም ስርዝ ድልዝ ያለው ሠነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ በተጨማሪም የጨረታ ማስያዣ (CPO) የሚያስገቡት ሠነድ ውስጥ ካልተካተተ ሠነዱ ውድቅ ይደረጋል፡፡
ሸ) ከተራ ቁጥር 1 እስከ ተራ ቁጥር 3 ድረስ የተዘረዘሩት ዕቃዎች በድርጅቱ የውስጥ አሠራር መሠረት በቅድሚያ የፅሁፍ የሽያጭ ውል ይደረጋል።
1) ተራ ቁጥር 1 እና 2 ላይ ላሉት ዕቃዎች የሽያጭ ውል የሚደረግባቸው ከጥቅምት 10/2018 ዓ/ም ጀምሮ ይሆናል
2) ከተ/ቁ 4 እስከ 7 ለተዘረዘሩት ዕቃዎች የጨረታው አሸናፊ እቃምቹን እንዲያነሳ ከተነገራቸው በኋላ በሶስት (3) የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ ገቢ በማድረግ እቃውን የማንሳት ግዴታ አለባቸው፡፡
3) በተራ ቁጥር 3 ላይ ላሉት ዕቃዎች ከአንድ በላይ የሆኑ ተጫራቾች ሊመረጡ ይችላሉ፡፡
ቀ) ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ሊገዙ በሚመጡበት ጊዜ ሊያሟሉ የሚገባቸው መስፈርቶች፡፡
1. የታደሠ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ (2017 ዓ/ም) (ለተዘረዘሩት ሁሉም የዕቃ ዓይቶች) ።
2. ከ ተራ ቁጥር 1,2 እና 3 ለተዘረዘሩት ዕቃዎች የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ሠርተፊኬት ሠነዱን በሚያስገቡበት ጊዜ ማቅረብ ይኖርባቸዋል ይህ ካልሆነ ሠነዱ ሙሉ በሙሉ ውድቅ ይደረጋል።
3. ማንነታቸውን የሚገልፅ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ ፤ ፓስፖርት ወይንም የታደሰ መንጃ ፈቃድ ማምጣት ይኖርባቸዋል፡፡ (ለተዘረዘሩት ሁሉም የዕቃ ዓይነቶች) ፡፡
የተጠቀሱትን መረጃዎች ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን የጨረታ ሠነድ በሚገዙበት ጊዜ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ይህን ለማያሟላ ማንኛውም ተጫራች ሠነድ የማንሸጥ መሆናችንን እንገልጻለን፡፡
በ) ተጫራቹ ህጋዊ ሰውነት ያለው ድርጅት በሚሆንበት በጨረታው ለመሳተፍ የቀረበው የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ መሆኑን የሚያስረዳ ሰነድ (በሚመለከተው አካል የተመዘገበና የጸደቀ የመመስረቻ ፅሁፍ እና/ወይም ቃለ ጉባኤ) እና የድርጅቱን የታደሰ የንግድ ፈቃድ ይዞ መቅረብ ይጠበቅበታል፡፡
ተ) የጨረታው አሸናፊ ባቀረበው ዋጋ መሰረት በጨረታ ማስታወቂያው ወይም በውሉ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ እቃውን ባይወስድ/ባያነሳ፤ ክፍያ ባይፈጽም፣ (ውል በሚያስፈልግበት ግዜ ውል ለመፈጸም ፈቃደኛ ባይሆን) ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ ጨረታው ወዲያውኑ ይሰረዛል፤ እንዲሁም ጨረታው በድጋሚ በሚወጣበት ወቅት የዋጋ ልዩነት ከመጣ ልዩነቱን እንዲከፍል ይገደዳል፤
ቸ) ማንኛውም አሸናፊ ያሸነፈውን ዕቃ በሚያነሳበት ጊዜ ዕቃዎቹን መምረጥ አይችልም፡፡
ኀ) በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ (Bid Bond) በሚቀጥሉት ሁለት (2) የሥራ ቀናት ተመላሽ ይሆናል፡፡
ነ) ድርጅቱ ጨረታውን በማንኛውም ግዜ በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ እና ሰነድ ለመግዛት እነዚህን ስልክ ቁጥሮች ይጠቀሙ፡፡
ስልክ ቁጥር :- +251-115-17-88-24 +251-115-17-87-81
የኢትዮጵያ አየር መንገድ
