በጉምሩክ ኮሚሽን የሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት ለቅ/ጽ/ቤቱ ለሰራተኞት ሰርቪስ አገልግሎት የሚሰጡ 04 /አራት/ ኮስተር ተሽከርካሪዎች፣ 01 (አንድ) ሃይሩፍ እና 02 (ሁለት) ሃይሉክስ ደብል ገቢና በአንድ ሎት ለሰመራ አየር ጠባይ ተስማሚ የሆኑ ወንበሮች ከጨርቅ የተሰራ እና ኤሲ (AC) ያላቸው በግልጽ ጨረታ ግዥ አወዳድሮ ለአንድ (01) ዓመት የሚቆይ ውል መያዝ ይፈልጋል።
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር፡-CC-SBO NCB/07/2017/2025
በጉምሩክ ኮሚሽን የሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት ለቅ/ጽ/ቤቱ ለሰራተኞት ሰርቪስ አገልግሎት የሚሰጡ 04 /አራት/ ኮስተር ተሽከርካሪዎች፣ 01 (አንድ) ሃይሩፍ እና 02 (ሁለት) ሃይሉክስ ደብል ገቢና በአንድ ሎት ለሰመራ አየር ጠባይ ተስማሚ የሆኑ ወንበሮች ከጨርቅ የተሰራ እና ኤሲ (AC) ያላቸው በግልጽ ጨረታ ግዥ አወዳድሮ ለአንድ (01) ዓመት የሚቆይ ውል መያዝ ይፈልጋል።
ስለሆነም ተሽከርካሪዎችን የሚያመለክተው የጨረታው ዝርዝር ሁኔታ በጨረታ ሠነዱ ላይ መመልከት ትችላላችሁ።
በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፤
- ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር አስገቢው ባለስልጣን የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ እና ተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፊኬት ማቅረብ አለባቸው።
- የጨረታ ማስከበሪያ ብር 70,000.00 (ሰባ ሺህ ብር) በባንክ የተመሰከረለት CPO ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ጋራንቲ ከጨረታ ሠነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሰመራ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የግዥና ፋይናንስ ቡድን ቢሮ አንደኛ ፎቅ በማቅረብ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ከሰኔ 11 ቀን 2017 ዓ.ም እሰከ ሰኔ 20 ቀን 2017 ዓ.ም ለተከታታይ ለ10 ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ መሆኑ ይታወቅ።
- ጨረታው ሰኔ 21 ቀን 2017 ዓ.ም በ4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዚሁ ቀን በ4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- የጨረታው አሸናፊ የመልካም ስራ አፈፃፀም ዋስትና 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) CPO በማስያዝ ከመስሪያ ቤቱ ጋር ውል ይፈራረማል።
- ጨረታውን የምናስተናግደው በእያንዳንዱ ተሽከርካሪ (car by car) ይሆናል።
- ተጫራቾች ከጨረታው ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ ሊኖረው አይገባም ካለውም ፓራፍ መደረግ አለበት።
- ተጫራቾች ከሚሞሉት ሰነድና ፖስታ ላይ የድርጅታቸው ማህተም እንዲሁም ስም፣ አድራሻ፣ ስልክ፣ ኢሜይል አድራሻ ማድረግ አለባቸው።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸው መኪናዎች ለእያንዳንዱ ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች ተመሣሣይ የሰርቪስ ዋጋ ቢያቀርቡ ቃለ ጉባኤ በመያዝ በእጣ የምንለይ መሆኑን እናሳውቃለን።
- ዘግይቶ የመጣ የተጫራች ፖስታ ተቀባይነት የለውም።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የጨረታ ሰነድ መሸጫና ጨረታ መክፈቻ ቦታ ሰመራ ጉ/ቅ/ፅ/ቤት ግዥና ፋይናንስ ቡድን አስተባባሪ 1ኛ ፎቅ
ስልክ ቆጥር :-033-3-66-88-39/ 033-3-66-15-67/ 09-17-35-11-51
በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የጉምሩክ ኮሚሽን ሰመራ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
