በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በጤና ጥበቃ ቢሮ የደብረሲና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በ2018 በጀት አመት ለሚፈፅማቸው ግዥዎች ማለትም ሎት 1. የሰራተኞች የትራንስፖርት ሰርቪስ አገልግሎት ግዥ፣ ሎት 2 የመድሃኒት ጭነት ከአዲስ አበባ እና ከደ/ብርሃን የኦከስጅን ስሊንደር ጭነት አገልግሎት ግዥ ለመፈፀም በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ከሀምሌ 1/2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሰኔ 30/2018 ዓ.ም ለሶስተኛ ወገን በኮንትራት ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡-01/2018
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በጤና ጥበቃ ቢሮ የደብረሲና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በ2018 በጀት አመት ለሚፈፅማቸው ግዥዎች ማለትም ሎት 1. የሰራተኞች የትራንስፖርት ሰርቪስ አገልግሎት ግዥ፣ ሎት 2 የመድሃኒት ጭነት ከአዲስ አበባ እና ከደ/ብርሃን የኦከስጅን ስሊንደር ጭነት አገልግሎት ግዥ ለመፈፀም በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ከሀምሌ 1/2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሰኔ 30/2018 ዓ.ም ለሶስተኛ ወገን በኮንትራት ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሰረት፡-
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር/ ያላቸውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- የሚሞሉት ጠቅላላ ዋጋ ከብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የጨረታ ሰነዱን ብር 150.00 /አንድ መቶ ሃምሳ ብር/ በመክፈል ከሆስፒታሉ ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 62 መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ያስገቡትን ጠቅላላ ዋጋ 2% ያክሉን ለሆስፒታሉ በCPO /በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው።
- ከብር 3.000.00 /ሶስት ሺህ ብር/ በላይ ለሚገዙ አገልግሎቶች 2% የመቁረጥ ግዴታ አለብዎት፡፡
- ለሰራተኞች ትራንስፖርት ጨረታ ተሽከርካሪው በወንበር (24) ሀያ አራት /ሰው/ እና በላይ የመጫን አቅም ያለው፡፡ እና የተሽከርካሪው የስሪት ዘመን እንደ ኤሮፓ አቆጣጠር 2010 እና ከዚህ ወዲህ የተመረተ፡፡
- ተጫራቾች የሚያስገቡት ዋጋ ለመኪናው የሚያስፈልጉ የተለያዩ ወጪዎችን እና የናፍጣ ክፍያ በራሱ የሚሸፈን መሆኑን ታሳቢ አድርጎ ይሆናል፡፡
- ለሰራተኞች ትራንስፖርት ጨረታ ለሚሳተፉ የስራ ጊዜው በመንግስት የስራ ሰዓት መግቢያና መውጪያ ጠዋት፣ ምሳ ሰዓትና ማታ አገልግሎት መስጠት ሲሆን ለጭነት አገልግሎት ጨረታ ደግሞ ጭነት በሚኖርበት ጊዜ ብቻ ይሆናል፡፡
- ለሰራተኞች የትራንስፖርት እና ለጭነት አገልግሎት ጨረታ የተሸከርካሪው ሊብሬ በተጫራቹ ስም የሆነ፣ ኢንሹራንስ እና ሶስተኛ ወገን የተገባለት እንዲሁም የቴክኒክ ምርመራ /ቦሎ/ ያሰራ መሆን አለበት፡፡
- ለሰራተኞች የትራንስፖርት ጨረታ ተሽከርካሪው በህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የተመዘገበ እና ለጭነት አገልግሎት ደግሞ በደረቅ ጭነት አገልግሎት የተመዘገበ መሆን አለበት፡፡
- ለሁለቱም ሎቶች የሚያቀርበት ሰነድ ላይ ሙሉ አድራሻቸውን፣ ስማቸውን፣ ፊርማቸውን እና የድርጅታቸውን ማህተም ማስቀመጥ አለባቸው።
- የሁለቱም ጨረታዎች አሸናፊ ሆኖ የተመረጠው ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለፀለት ከ5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ 10% ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ በCPO /በጥሬ ገንዘብ/ በማስያዝ ውል መውሰድ የሚችል መሆን ይኖርበታል። የሁለቱም ውለታዎች እንደ አስፈላጊነቱ በሩብ አመት፣ በግማሽ አመት ወይም የአንድ በጀት አመት ውል የሚፈፀም ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ነጣላ ዋጋና ጠቅላላ ዋጋ ዝርዝር አባሪ ዶክሜንቶችን ጨምሮ የጨረታ ሰነዱን ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በፖስታ አሽገው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ክፍት ሆኖ የሚቆየው የጨረታ ማስታወቂያው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆይና በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ይታሸጋል፡፡
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ላይ በሆስፒታሉ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታዉ የሚከፈት ይሆናል።
- ለሁለቱም ሎቶች ተጨማሪ መረጃዎችን ከጨረታው መመሪያና ከዋጋ መሙያ ላይ ማየት ይቻላል፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የመንግስት የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ ባለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0913869679፣ 0925402088 ወይም 0924854239 ደውለው ይጠይቁ፡፡
አድራሻ፡- ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ በሚወስደው ዋና መንገድ ላይ 190 ኪሎ ሜትር ደብረሲና ከተማ
የደብረሲና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል
