Tender Detail

Tender Details


በደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን የሚገኘው የመገናኛ ሁለገበ/ኅ/ስራ ማህበራት ዩኒየን ኃላ/የተወሰነ የሂሳብ አያያዝን ለማዘመን 1) የፕስትሪ ሶፍት ዌር ኮምፒውተሮች ላይ መጫን፤ 2) ለሂሳብ ባለሙያዎች የፒስትሪ ሂሳብ አያያዝ ለ10 ቀን በስራ ላይ የተግባር ልምምድ ስልጠና መስጠት፤ 3) የ2017 ዓ.ም የዩኒየኑን አጠቃላይ የገቢና ወጪ የሂሳብ እንቅስቃሴ ሙሉ ምዝገባ አድርጎ እና የዩኒየኑን ሙሉ ፋይናንሻል ሪፖርት አዘጋጅቶ ለዩኒየኑ ማስረከብ ሲሆን ከላይ ከ 1 እስከ 3 የተዘረዘሩትን አገልግሎቶች በግልፅ ጨረታ ዘዴ አወዳድሮ አገልግሎቱን ማግኘት ይፈልጋል።


 

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን የሚገኘው የመገናኛ ሁለገበ//ስራ ማህበራት ዩኒየን ኃላ/የተወሰነ የሂሳብ አያያዝን ለማዘመን 1) የፕስትሪ ሶፍት ዌር ኮምፒውተሮች ላይ መጫን፤ 2) ለሂሳብ ባለሙያዎች የፒስትሪ ሂሳብ አያያዝ 10 ቀን በስራ ላይ የተግባር ልምምድ ስልጠና መስጠት፤ 3) 2017 . የዩኒየኑን አጠቃላይ የገቢና ወጪ የሂሳብ እንቅስቃሴ ሙሉ ምዝገባ አድርጎ እና የዩኒየኑን ሙሉ ፋይናንሻል ሪፖርት አዘጋጅቶ ለዩኒየኑ ማስረከብ ሲሆን ከላይ 1 እስከ 3 የተዘረዘሩትን አገልግሎቶች በግልፅ ጨረታ ዘዴ አወዳድሮ አገልግሎቱን ማግኘት ይፈልጋል። በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተወዳዳሪዎች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።

  1. በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችሉ።
  2. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ጥቅል ዋጋ መሰረት በማድረግ የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ 2% በባንክ CPO (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ /ዋስትና አስይዘው ጨረታ ከመከፈቱ በፊት ከጨረታ ሰነዱ ጋር በፖስታ አሽገው ማስገባት አለባቸው። ከዩኒየኑ በጥሬ ገንዘብ በገቢ ደረሰኝ የሚያሲዙ ከሆነ የገቢ ደረሰኙን ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከሚወዳደሩበት ሰነድ ጋር አሽገው ማቅረብ አለባቸው።
  3. የግዥው መጠን 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ዋጋ የሚሆን ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ እንዳይሰበሰብባቸው ፈቃድ የተሰጣቸው (በግብር አዋጁ ከግብር ነጻ ከሆኑ) አቅርቦቶች ካልሆነ በስተቀር በግዥው የሚሳተፉ ማንኛውም ተጫራቾች በተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ መረጃ ማቅረብ አለባቸው። እንዲሁም ዋጋ ሲሞሉ እና (ሲፒኦ) ሲያሲይዙ ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት። ቫት የሚጠይቀው የአንዱ ወይም በጥቅል /ሎት/ የሚገዛው እቃ እንጂ በአንድ ማስታወቂያ ለወጡ አለመሆኑ ይታወቅ።
  4. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 100 ብር በመክፈል ከዩኒየኑ የጨረታ ሰነዱን መግዛት አለባቸው፡፡ እንዲሁም የተጫራቾች መመሪያ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዞ ይሰጣል።
  5. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የስራ ዝርዝር አገልግሎት ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው የእንዱንና ጠቅላላ ዋጋውን ሞልተው በፖስታ አሽገው ከዩኒየኑ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በወቅቱ ማስገባት አለባቸው።
  6. አሸናፊው ተወዳዳሪ የሚለየው በጥቅል ዋጋድምር በመሆኑ በጨረታ ሰነዱ ላይ የተዘረዘሩትን ሁሉንም የአገልግሎት አይነቶች በዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱ ላይ ተጫራቹ መሙላት አለበት።
  7. ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ቅዳሜ እስከ 630 ሰዓት ጨምሮ የጨረታ ሰነዱ ተሸጦ 10ኛው ቀን 800 ሰዓት የጨረታ ማስገቢያ ሳጥኑ ታሽጎ በዚሁ እለት 815 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ይከፈታል። ሆኖም ግን 10ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ ቀን ከላይ በተገለጸው ተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
  8. አሸናፊው ተጫራች ተወዳድሮ ያሸነፈበትን ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በሲፒአ ወይም በጥሬ ገንዘብ አስይዞ 5 ቀን ውስጥ ከዩኒየኑ /ቤት ቀርቦ ውል መውሰድ አለበት።
  9. አሸናፊው ተወዳዳሪ የፒስትሪ ሶፍት ዌር /አገልግሎት እና ስልጠና ደብረታቦር ከተማ ከዩኒየኑ /ቤት ድረስ ተገኝቶ መስጠት አለበት።
  10. ዩኒየኑ ያወጣውን ግልጽ ጨረታ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው።
  11. ቅዳሜ ከሰዓት በፊት ወይም ግማሽ ቀን የዩኒየኑ የስራ ቀን ነው።
  12. ተጨማሪ መረጃ ክፈለጉ በስልክ ቁጥር 058-4-41-13-36 እና 058-1-41-9927 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

አድራሻ፡- ደብረታቦር ከተማ ጸደይ ዋና ባንክ እንደኛ ፎቅ       

 

መገናኛ ሁለገብ የገበ////ዪኒየን ኃላ/የተወሰነ

 

Save Tender