ፀደይ ባንክ አ.ማ. በአዲስ አበባ ከተማ ልደታ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 07(ሰንጋተራ አካባቢ) ባስገነባው 4B+G+M+25 ህንጻ ውስጥ፡-ከምድር ወለል ጀምሮ እስከ 6ኛ ፎቅ ለንግድ ስራ (ለሱቅ፣ ለሬስቶራንት፣ ለፋርማሲ፣ ለሜዲካል ሴንተር፣ ለውበት ሳሎን፣ ካፌ፣ ሱፐር ማርኬት፤ ሾዉ ዲስፕለይ ሩም ወዘተ) አገልግሎት የተዘጋጁ ክፍሎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል።
የህንፃ ኪራይ የጨረታ ማስታወቂያ
ፀደይ ባንክ አ.ማ. በአዲስ አበባ ከተማ ልደታ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 07(ሰንጋተራ አካባቢ) ባስገነባው 4B+G+M+25 ህንጻ ውስጥ፡-ከምድር ወለል ጀምሮ እስከ 6ኛ ፎቅ ለንግድ ስራ (ለሱቅ፣ ለሬስቶራንት፣ ለፋርማሲ፣ ለሜዲካል ሴንተር፣ ለውበት ሳሎን፣ ካፌ፣ ሱፐር ማርኬት፤ ሾዉ ዲስፕለይ ሩም ወዘተ) አገልግሎት የተዘጋጁ ክፍሎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል።
በመሆኑም፡-
- ተጫራቾች የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ ፀደይ ባንክ ለገሀር ቅርጫፍ ወይም በማናኛውም የፀደይ ባንክ ቅርንጫፍ በመክፈል የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሐምሌ 01 ቀን 2017 ዓ.ም ጨረታው እሰከሚዘጋበት ድርስ መ/ቤቱ በመቅረብ ዘውትር በስራ ስዓት ክሰኞ እስከ አርብ ከ2፡00 እስከ 11፡00 ሰዓት እና ቅዳሜ እስከ 6፡00 ሰንጋተራ በሚገኘዉ ፀደይ ባንክ አማ ዋና መ/ቤት 16ኛ ፎቅ ግዠ ክፍል መውሰድ ይችላሉ። ጨረታው የሚከፈትበት ቦታና ሰዓት ሰንጋተራ አካባቢ በሚገኘዉ ፀደይ ባንክ ኤማ ዋና መ/ቤት 5ኛ ፎቅ በሚገኘው የስብሰባ አዳራሽ ሲሆን የጨረታው መዝጊያ ቀን ሐምሌ 01 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ሲሆን የጨረታ መክፈቻ በተመሳሳይ ቀን ሐምሌ 01 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ላይ ይሆናል።
- ተጫራቾች ከአንድ በላይ በሆኑ ክፍሎች መሳተፍ ይችላሉ። ሆኖም የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚወዳደሩበትን ክፍሎች ካሬ ሜትር ጠቅላላ የስድስት ወር የቅድሚያ ክፍያ የክራይ ዋጋ መነሻ በማድረግ 2% ወይም የጠቅላላ ዋጋው 2% ከብር 500,000.00 የሚበልጥ ከሆነ ብር 500,000.00 በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) በፀደይ ባንክ አማ ስም ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች ነጋዴዎች ከሆኑ የታደሰ እና አግባብነት ያለው የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶች ከሆኑ የታደሰ የምዝገባ ሰነድ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራጮች ህንጻዉን (ክፍሉን) ለምን ዓላማ እንደሚከራዩት መግለጽ አለባቸዉ።
- ተጫራቾች ለኪራይ የቀረቡ ክፍሎችን በተዘጋጀዉ የዋጋ ማቅረቢያ ሰንጠረዥ ላይ በተገለፀዉ ቦታ ከሰኔ 16 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በስራ ቀን እና ሰዓት አዲስ አበባ ህንፃው ባለበት ቦታ በመገኘት ማየት ይችላሉ።
- የጨረታው አሸናፊ የሚሆነዉ ለክፍሎች በተሰጣቻው መለያ ቁጥር መሰረት በሜትር ካሬ ከመነሻው ዋጋ በላይ ከፍተኛ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች ይሆናል።
- ተጫራቾች በፖስታቸዉ ላይ ስም፣ ፊርማና ስልክ ቁጥር መፃፍ አለባቸዉ።
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 18 78 21 88 /09 11 38 37 13 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
- ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- አዲስ አበባ ከተማ ፤ ሰንጋተራ አካባቢ በሚገኘው የባንኩ ዋና መ/ቤት ህንጻ 16ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 09
ፀደይ ባንክ አ.ማ
