የአ/አበባ ፖሊስ በ2017 በጀት ዓመት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር AAPC NCB 0010/2017 ዓ/ም
የአ/አበባ ፖሊስ በ2017 በጀት ዓመት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት የሚፈልግ ሲሆን፡-
|
ሎት |
የጨረታ ዓይነት |
የናሙና መለያ |
የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ መጠን |
|
|
001 |
የእስረኛ ቀለብ |
በኮሚሸኑ ፍላጎት መሰረት |
40,000 |
00 |
|
002 |
የአስክሬን መጠቅለያ ላስቲክ |
በኮሚሽኑ ፍላጎት መሰረት ሆኖ የኮሚሽኑን ሳንፕል በማየት ናሙና የሚቀርብበት |
40,000 |
00 |
|
003 |
Supply design installation commissioning and testing network access control (NAC) solution ግዥ |
በኮሚሸኑ ስፔስፊኬሽን መሰረት |
200,000 |
00 |
|
004 |
175-180 ሲሲ ጉልበት ያላቸው ሞተር ሳይክል |
በኮሚሸኑ ስፔስፊኬሽን መሰረት |
40,000 |
00 |
|
005 |
የታሸገ ውሃ ግዥ |
በኮሚሽኑ ፍላጎት መሰረት ሆኖ ለ01 ዓመት የሚቆይ በኮሚሽኑ ፍላጎት መሰረት |
40,000 |
00 |
|
006 |
ለውሾች ቀለብ ሚሆን አጥንት የሌለው ስጋ |
በኮሚሸኑ ስፔስፊኬሽን መሰረት |
150,000 |
00 |
|
007 |
የተለያዩ መድሃኒቶች፣ የላብራቶሪ ሬኤጀንት እና የተለያዩ የህክምና መሳሪያዎች |
በኮሚሸኑ ስፔስፊኬሽን መሰረት |
100,000 |
00 |
|
008 |
በኤሌትሪክ የሚሰሩ ሞተር ሳይክሎች |
በኮሚሸኑ ስፔስፊኬሽን መሰረት |
100,000 |
00 |
|
009 |
ለሰነድ ምርመራና የሚሆን የቴክኖሎጂ ውጤቶች ግዥ ለሰነድ የሚረዳ መሳሪያ document forensic tools |
በኮሚሸኑ ስፔስፊኬሽን መሰረት |
300,000 |
00 |
|
010 |
የዘመናዊ በኬሚካል የሚሰራ ፎቶ ፕሪንተር |
በኮሚሸኑ ስፔስፊኬሽን መሰረት |
300,000 |
00 |
- በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው መሆን እና በዘርፉ የተሰማሩ ለመሆናቸው በጀርባው ይመልከቱ የሚል ፅሁፍ በግልፅ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
- የታደሰ የዘመኑን ንግድ ፍቃድ እና የታደሠ ንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- የመንግስት መ/ቤቶች ለሚያወጡት ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የአቅራቢዎች የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ክሊራንስ ማቅረብ አለበት፡፡
- አማራጭ ዋጋ በዚህ ጨረታ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ የጨረታ ውጤቱ እንደታወቀ ተመላሽ የሚሆን በሎቱ ፊት ለፊት የተቀመጠውን የገንዘብ መጠን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለአዲስ አበባ ፖሊስ ተብሎ በተዘጋጀው ከባንክ በተመሰከረለት ሲ.ፒ.ኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ቴክኒካል ሰነዶችንና የዋጋ ማቅረቢያዎችን /ፋይናሻል/ ሰነዶች በተለያየ ፖስታ ታሽጎ ለየብቻ መቅረብ አለባቸው።
- ማንኛውንም ተጫራቾች የሚያስገባው ሰነድ ፋይናሻል እና ቴክኒካል የጨረታ ሰነድ አንድ ኦሪጅናልና አንድ ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማሸግ በፖስታው ላይ የጨረታ ሰነዱን ቁጥር የሚጫረትበትን ዕቃ አይነት በትክክል መፃፍ እንዲሁም በፖስታው ላይ ማህተም በመምታት ማስገባት ያለበት ሲሆን፣ ሰረዝ ድልዝ በፍሉድ የጠፋ ሰነድ ዋጋ ያልተሞላበት ዝርዝር ተቀባይነት የሌለው መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚያሲዙት ሲ.ፒ.ኦ. ከቴክኒክ ሰነዶችጋር በአንድ ላይ ታሽገው መቅረብ አለባቸው፡፡
- በጨረታ አሸናፊ የሆኑ ድርጅቶች ዕቃውን ወይም አገልግሎቱን በራሳቸው ትራንስፖርት አ/አበባ ከተማ ውስጥ በሚገኘው የኮሚሽኑ ዋና መስሪያ ቤት ግምጃ ቤት ወይም በከፍል 6 በፍላጎት መግለጫው በተጠቀሰው የማስረከቢያ ቦታ ድረስ በማምጣት ማስረከብ አለባቸው፣
- በጨረታ ሰነድ በክፍል 6 ውስጥ በሚገኘው የፍላጎት መግለጫ ላይ በሚገለፀው መሰረት ጨረታ ሰነዱ ላይ በቀረበው መሰረት ናሙና ማቅረብ አለበት፡፡
- ተጫራቾች ያቀረቡት ናሙናም ሆነ አሸናፊ መሆናቸው ሲረጋገጥ ያቀርቡአቸው ዕቃዎች ኮሚሽኑ ባወጣው ፍላጎት መግለጫ /specification/መሰረት መሆኑን በኮሚሽኑ የጥራት ኮሚቴ ወይም በኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ኤጀንሲ አማካኝነት የሚረጋገጥ ይሆናል።
- ተጫራቾች አራዳ ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን ከፍ ብሎ በሚገኘው የኮሚሽኑ ዋና መስሪያ ቤት 5ኛ ፎቅ ግዢ ጽ/ቤት ቢሮ ቀርበው በእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፣
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 15 የስራ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ እንዲሁም በማግስቱ በ16ኛው ቀን እስከ ጠዋት 4፡30 ሠዓት ድረስ ጨረታው ክፍት ሆኖ ስለሚቆይ በኮሚሽኑ ግዢና ፋይናንስ 5ኛ ፎቅ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
- በጨረታ ሰነዱ ክፍል 2 ላይ በሚጠቀሰው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ 5፡00 ሰዓት ሲሆን በመ/ቤቱ 5ኛ ፎቅ ትንሹ አዳራሽ ቢሮ ቁጥር 512 ይከፈታል፣
- የጨረታው መክፈቻ የስራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው መደበኛ የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው 4፡30 ሰዓት ታሽጎ 5፡00 ሲሆን ይከፈታል፡፡
- ዘግይተው የሚመጡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስ/ቁጥ 011 862 5800 (011 111 0448)
የአ/አበባ ፖሊስ
