Tender Detail

Tender Details

  • Company Development Bank of Ethiopia (የኢትዮጵያ ልማት ባንክ)
  • Address ካዛንቺስ ሾንጌ ህንጻ 2ኛ ፎቅ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0115 57 80 88
  • Websitehttps://dbe.com.et/
  • Deadline09 Jul 2025, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price
  • opening date2025-07-10 00:00:00
  • Categories Land, House, Building And Warehouse Rent

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሰሜን ምስራቅ አዲስ አበባ ዲስትሪክት፤ ደቡብ ምዕራብ አዲስ አበባ ዲስትሪክት እና ደብረ-ብርሃን ዲስትሪክት ግዴታቸውን ከማይወጡ የካፒታል ዕቃ ተከራዮች የሚረከባቸውን ማሽኖች ተረክቦ የሚያስቀምጥበት መጋዘን በጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል፡፡


 

የመጋዘን ኪራይ ጨረታ ማስታወቂያ

 

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሰሜን ምስራቅ አዲስ አበባ ዲስትሪክት፤ ደቡብ ምዕራብ አዲስ አበባ ዲስትሪክት እና ደብረ-ብርሃን ዲስትሪ ግዴታቸውን ከማይወጡ የካፒታል ዕቃ ተከራዮች የሚረከባቸውን ማሽኖች ተረክቦ የሚያስቀምጥበት መጋዘን በጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ በአዲስ አበባና በሸገር ከተሞች ውስጥ የመጋዘን ኪራይ አገልግሎት የምትሰጡ ግለሰቦችና ድርጅቶች የምታከራዩበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሐምሌ 02 ቀን 2017 . ድረስ በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 200 ሰዓት እስከ 11:00 ሰዓት ድረስ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሰሜን ምስራቅ አዲስ አበባ ዲስትሪክት 2 ወለል ላይ በሚገኘውና ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ትችላላችሁ ጨረታው ሐምሌ 03 ቀን 2017 . ከጠዋቱ 300 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ለኪራይ የሚቀርቡ መጋዘኖች፡-

  1. የመጋዘኑ ስፋት 1500 . ያላነሰ፤ ቁመቱ ቢያንስ 6 ሜትርና ሰፊ ግቢ ያለው መሆን አለበት፤
  2. ግንባታቸው ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቀ መሆን ይኖርባቸዋል፤
  3. የመጋዘኑ በር ዕቃ የጫነ መኪና ዕቃ የሚጭንና የሚያወርድ ማሽን ገብቶ ያለምንም የቦታ ጥበት ማንቀሳቀስ የሚያስችል፤
  4. ከዋና መንገድ (ከመሀል ከተማ) ብዙ ያልራቀና መሠረተ ልማቱ የተሟላ መሆን አለበት፤
  5. ውሀ፣ መብራት እና የጥበቃ መኖሪያ ቤት ቢኖረው ተመራጭ ይሆናል፤
  6. የኪራይ ዘመኑ ቢያንስ 3 ዓመትና ከዚያ በላይ መሆን አለበት፡፡
  7. ተጫራቾች የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታና የታደሰ የግብር ከፋይ ማረጋገጫ ሰነድ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፤
  8. ጨረታውን ያሸነፈ ጨረታውን ማሸነፉ ከተነገረው ቀን ጀምሮ በአንድ ሣምንት ጊዜ ውስጥ አስፈላጊውን ሁሉ አሟልቶ የውል ስምምነት ተፈራርሞ መጋዘኑን ማስረከብ አለበት፡፡
  9. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ

  • ካዛንቺስ ሾንጌ ህንጻ 2 ፎቅ
  • ለበለጠ መረጃ . 0115 57 72 33 ደውለው ይጠይቁ።

 

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሰሜን ምስራቅ አዲስ አበባ ዲስትሪክት

 

Save Tender