Tender Detail

Tender Details

  • Company በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 8 አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-8-53-89-75
  • Website
  • Deadline11 Jul 2025, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price300.00
  • opening date2025-07-11 00:00:00
  • Categories Land, House, Building And Warehouse Rent

በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 08 አስተዳደር ቤቶች ጽ/ቤት ስር የሚተዳደሩ በሾላ ገበያ እና ከፊል ንግድ ቤቶች ውስጥ ከሚገኙ 39 የንግድ ሱቆችን አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡


 

የንግድ ሱቆች የኪራይ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡- 02/2017 .

 

በየካ /ከተማ ወረዳ 08 አስተዳደር ቤቶች /ቤት ስር የሚተዳደሩ በሾላ ገበያ እና ከፊል ንግድ ቤቶች ውስጥ ከሚገኙ 39 የንግድ ሱቆችን አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሰረት በጨረታው መወዳደር የሚቻለው፡-

  1. በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውስጥ በራሱ ስም ሆነ በትዳር አጋሩ ስም የመንግስት ንግድ ቤት የሌለው /የሌላት/፡፡
  2. የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ መሆኑን የሚገልጽ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ እና ፋይዳ መታወቂያ ያለው/ ያላት/፡፡
  3. የጨረታው ሰነድ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል በየካ /ከተማ ወረዳ 08 ፋይናንስ /ቤት መግዛት ይኖርባቸዋል
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ ብር ተጫራቾች ለኪራይ ከሚሞሉት የአመት ኪራይ ላይ 20% ብር በየካ ወረዳ 08 ፋይናንስ /ቤት ስም በሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች ለጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ ብቻ በመጠቀም በካሬ የሚገዙበትን የመወዳደሪያ ዋጋ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ነገር ግን በሌላ ቅጽ የሚጠቀሙ ተጫራቾችን ጨረታ ውስጥ እዳይሳተፉ ያደርጋል፡፡
  6. የንግድ ሱቆቹ ዝርዝር ሰንጠረዥ ውስጥ የተገለጹ ልዩ መለያ የቤት ቁጥር እና የሚከራዩበትን በካሬ መነሻነት ዋጋ የቀረቡ ሲሆን ተጫራቾች ከዛ መነሻ ዋጋ በመነሳት የራሳቸውን ዋጋ በተቀመጠው የዋጋ መሙያ ላይ በካሬ መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ተጫራቾች በጨረታ መወዳደር የሚችሉት በአንድ የጨረታ ሰነድ ላይ ብቻ ነው፡፡
  8. ስማቸውን፣ አድራሻቸውን እና ፊርማቸውን በእያንዳንዱ ሰነድ በመፈረም ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ (ማሻሻያ) ማድረግ እንዲሁም ከጨረታ እራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
  10. ተጫራቾች ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች አሟልተው በታሸገ ፖስታ አንድ ኦሪጅናል አንድ ኮፒ በወረዳ 08 ቤቶች አስተዳደር /ቤት ቢሮ ቁጥር 06 ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  11. ጨረታው የሚዘጋበት ቀን 11ኛው የስራ ቀን የስራ ቀን ካልሆነም በሚቀጥለው የስራ ቀን 400 ሰዓት ተዘግቶ 430 ሰዓት ህጋዊ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በወረዳ 08 ወጣት ማእከል አዳራሽ ይከፈታል፡፡
  12. በጨረታ ያሸነፈው አካል ማሸነፉን እንደተገለጸለት 15 ቀን ውስጥ በመስሪያ ቤቱ መመሪያ መሰረት ውል መፈጸም ይኖርበታል፡፡
  13. ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርቡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም፡፡
  14. ለጨረታ የወጡ የንግድ ሱቆቹን ማየት የሚቻለው ጨረታው ከወጣበት ካሉት ቀናቶች ውስጥ ማክሰኞ እና ሃሙስ 300 እስከ 600 ሰዓት እና ከሰዓት 800 ሰዓት እስከ 1100 ሰዓት ብቻ የምናሳይ ስለሆነ በተጠቀሱት የስራ ቀን እና ሰዓት እየመጡ ማየት የሚችሉ ይሆናል፡፡
  15. /ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡-011-8-53-89-75 መደወል ይችላሉ።

 

በየካ /ከተማ ወረዳ 8 አስተዳደር ፋይናን ኢኮኖሚ ልማት /ቤት

 

Save Tender