የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ጥራታቸውን የጠበቁ ቋሚና አላቂ ዕቃዎችን በቅድመ ብቃት ማረጋገጫ ማጣሪያ ግልጽ ጨረታ መሰረት በመለየት በአቅራቢነት በመመዝገብ በወቅቱና በጥራት ዕቃዎችን ሊያቀርቡ የሚችሉትንና በቀጣይና በዘላቂነት ከኮርፖሬሽኑ ጋር አብሮ ለመስራት ፈቃደኛ የሆኑ ድርጅቶችን በመለየትና በማወዳደር ለቀጣይ ውድድር መጋበዝ ይፈልጋል።
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የቅድሚያ ብቃት ማረጋገጫ ማጣሪያ ግልፅ ጨረታ ቁጥር ግጨ/ቅብማማ02/2017
የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የሀገሪቷ ቁልፍ የመሰረተ ልማት ፍላጎቶች በሆኑት በመንገድና ድልድይ፣ በውኃና ኢነርጂ፣ በህንጻና ከተማ ልማት እንዲሁም በሌሎች የሲቪል ምህንድስና ሥራዎች በሚፈለገው ጊዜ፣ መጠንና ጥራት በማቅረብ በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ዘርፍ በዲዛይንና በግንባታ ሥራዎች መስክ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኝ የመንግስት የልማት ድርጅት ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በጂኦቴክኒካልና ጂኦሎጂካል ሥራዎች፣ በቅየሳ፣ በላቦራቶሪ ምርመራና ሥልጠና መስክ አገልግሎቶችን እየሰጠ ሲሆን፤ ኮርፖሬሽኑ የተቋቋመበትን ዓላማ ከግብ ለማድረስ በግብዓትነት የሚያስፈልጉ ጥራታቸውን የጠበቁ ቋሚና አላቂ ዕቃዎችን በቅድመ ብቃት ማረጋገጫ ማጣሪያ ግልጽ ጨረታ መሰረት በመለየት በአቅራቢነት በመመዝገብ በወቅቱና በጥራት ዕቃዎችን ሊያቀርቡ የሚችሉትንና በቀጣይና በዘላቂነት ከኮርፖሬሽኑ ጋር አብሮ ለመስራት ፈቃደኛ የሆኑ ድርጅቶችን በመለየትና በማወዳደር ለቀጣይ ውድድር መጋበዝ ይፈልጋል።
በመሆኑም፡-
- ተመዝጋቢዎች አግባብነት ያለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያሳይ የምስክር ወረቀት የሚያቀርቡ፣ ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ እንደዚሁም በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተካተቱ እና መመዝገባቸውን የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይገባቸዋል።
- ተመዝጋቢዎች የድርጅታቸውን አሁናዊ ገፅታ የሚያሳይ ፕሮፋይል፣ የሥራ አፈጻጸምን የሚገልፅ ማስረጃ፣ በኦዲት የተረጋገጠ የትርፍ እና ኪሳራ የሂሳብ መግለጫ የቅርብ ዓመታት፣ ከጥራት (ISO Certificate) እና ብቃት ጋር የተያያዙ ሌሎች መረጃዎቸ ማስያዝ ይችላሉ።
- ተወዳዳሪዎች የሚመዘገቡባቸው የውድድር ዘርፍ
|
ምድብ |
የዕቃው ዝርዝር |
|
1 |
ጠቅላላ እና የልዩ ህክምና አገልግሎት |
|
2 |
የተሽከርካሪዎች ኪራይ አገልግሎት |
|
3 |
የጥበቃ አገልግሎት |
|
4 |
የጽዳትና ንጽህና አገልግሎት |
|
5 |
የሆቴል እና የካፍቴሪያ አገልግሎት |
- ተወዳዳሪዎች በጨረታ ሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን ሙሉ አድራሻቸውን፣ ፊርማቸውን እና ድርጅታቸውን ማህተም ማስፈር አለባቸው።
- ተመዝጋቢዎች ጨረታው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ዕለት አንስቶ ለተከታታይ 10 (አስር) ቀናት ክፍት ሆኖ ስለሚቆይ ዘወትር በሥራ ሰዓት ኮርፖሬሽኑ ያዘጋጀውን ፎርም (ቅጽ) በመውሰድ አስፈላጊውን የድርጅታችሁን መረጃዎች በመሙላት፣ ፊርማና ማኅተም በማድረግ ከታች በተጠቀሰው አድራሻ ሰነዳቸውን በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይችላሉ።
አድራሻ፡- የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን
ሕንጻ 1 4ኛ ፎቅ፣ በኮርፖሬት አገልግሎቶች ቢሮ፣ ኮርፖሬት ግዥ ቡድን
ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05
ስልክ ቁጥር +251118720722
ኢትዮጵያ አዲስ አበባ
የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን
