Tender Detail

Tender Details

  • Company Addis Ababa City Administration Youth and Sports Bureau (የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ)
  • Address ፍላሚንጎ ምርጫ ቦርድ አጠገብ ባ/ኪ/ቱ ህንፃ ላይ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0118-12-07-78
  • Websitehttps://addisyouthandsport.gov.et/
  • Deadline18 Jul 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • opening date2025-07-18 00:00:00
  • Categories Land, House, Building And Warehouse Rent

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ስር የሚገኘው የራስ ኃይሉ ስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል ለስፖርት ባርና ሬስቶራንት አገልግሎት ላይ የሚውል 164.3 ካሬ ሜትር ስፋት ያለውን ንግድ ቤት ለሚፈልጉ ተጫራቾች በጨረታ አወዳድሮ ለ3 አመት ማከራየት ይፈልጋል፡፡


 

በድጋሚ የወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የስፖርት ባርና ሬስቶራንት የጨረታ ቁጥር፡- 02/2017 .

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ስር የሚገኘው የራስ ኃይሉ ስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል ለስፖርት ባርና ሬስቶራንት አገልግሎት ላይ የሚውል 164.3 ካሬ ሜትር ስፋት ያለውን ንግድ ቤት ለሚፈልጉ ተጫራቾች በጨረታ አወዳድሮ 3 አመት ማከራየት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከታች የተገለጸውን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾችን በማወዳደር ወደ ስራ ማስገባት ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሰረት በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡

  1. ተጫራቾች ከጨረታ ሰነድ ጋር ማንነታቸው የሚገልፅ ትክክለኛነቱ የተረጋገጠ መታወቂያ ፎቶ ኮፒ ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. በዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ የተጫራቹ ወይም የህጋዊ ወኪሉ ስም እና ፊርማ ማህተም ያረፈበት መሆን አለበት፡፡
  3. ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው ጨረታ ሰነድ በራስ ኃይሉ የስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል 1 ፎቅ ላይ ከአስ/ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 2 ቀርበው የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ/ ብር ከፍለው መግዛት ይጠበቅባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች የገዙትን የጨረታ ሰነድ በመሙላት ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ሰነዱን በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦሪጅናል ፎቶ ኮፒ አድርጎ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ሳጥን ውስጥ መጨመር ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የራስ ኃይሉ የስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል ስም የተሰራ ሲፒኦ 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/ ከጨረታ ፖስታ ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ተጫራቾች ከገዙት ጨረታ ሰነድ ውጭ ተሞልተው ለሚመጡ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
  7. የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት በአስረኛው የስራ ቀን 8:00 ሰዓት ላይ ታሽጎ 830 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በራስ ኃይሉ የስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል 1 ፎቅ ላይ በግልፅ ይከፈታል፡፡
  8. ከተባለው ቀንና ሰዓት በኋላ የሚመጣ የጨረታ ሰነድ ውድቅ ይሆናል፡፡
  9. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

 

አድራሻ፡- አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ህንፃ አጠገብ ወይንም ከመድኃኒዓለም አጠቃላይ 2 ደረጃ /ቤት ከሚገኘው አደባባይ ወደ ግሩም ሆስፒታል በሚወስደው አስፋልት መንገድ በስተግራ 100 ሜትር ገባ ብሎ፡፡

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የራስ ኃይሉ ስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማእከል

 

Save Tender