የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት የትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።
የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት የትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 01/18
ድርጅታችን የገዛውን ፓልም የምግብ ዘይት፤ ሸቀጣ ሸቀጥ፤ ስኳር፤ ሲሚንቶ እና የኢንዱስትሪ ጨው መነሻውን የፖልም የምግብ ዘይት ከእንዶዴ እና ከጅቡቲ፤ ሸቀጣ ሸቀጥ አ/አበባ ከሚገኘው የድርጅቱ መጋዘኖች፤ ለስኳር ከሁሉም የስኳር ፋብሪካዎች እና አ/አበባ ከሚገኘው መጋዘኖቻቸው፤ ሲሚንቶ ከሁሉም የሲሚንቶ ፋብሪካዎች እና ኢንዱስትሪ ጨው ከሱማሌ ክልል አፍሬራ ዞን ሀርገሌ ዩኦ ጨው አቅራቢ ማህበራት እና ከአፋር ክልል አፍደራ ጨው አቅራቢ ማህበራት ለተለያዩ በክልል ወደ ሚገኙት የድርጅቱ ቅ/ፎች ለማጓጓዝ በግልፅ ጨረታ የትራንስፖርት አገልግሎት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም በጨረታው መካፈል የሚፈልጉ ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟላ ተጫራቾች በጨረታው መካፈል የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፤ የብቃት ማረጋገጫ፤ ታክስ ክሊራንስ ሠርተፍኬት እና የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሠርተፍኬት ያላቸው መሆን ይገባቸዋል።
- ተጫራቾች ለጨረታው የተዘጋጀውን ዝርዝር የጨረታ ሰነዱ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ፒያሳ ቢስ መብራት አካባቢ/ አትክልት ተራ/ ከሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት ከሎጀስቲክስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች ፓልም የምግብ ዘይት ማጓጓዝ የጨረታ ማስከበሪያ ብርፓልም የምግብ ዘይት ብር 300,000.00 (ሶስት መቶ ሺ ብር) ለሸቀጣ ሸቀጥ ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺ ብር) ለስኳር ተጫራቾች ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺ) ሲሚንቶ ተጫራቾች ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺ) እና ኢንዱስትሪ ጨው ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺ) በባንክ በተመሰከረ የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ብቻ ከትራንስፖርት ታሪፍና ከብቃት ማረጋገጫ ማስረጃዎች ጋር ተያይዞ መቅረብ ይኖርበታል።
- የጨረታ መወዳደሪያ ዋጋቸውንና ከላይ የተጠቀሱ ህጋዊ ሰነዶችን በታሸገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦርጅናል እንዲሁም አንድ ኮፒ በማድረግ እና በአንድ ፖስታ በማሸግ እስከ ሀምሌ 11 ቀን 2017 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ጨረታው ሀምሌ 11 ቀን 2017 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡10 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ተጫራቾች በጨረታው መመሪያ ላይ የተገለፀውን ደንብና ግዴታ በሙሉ የመፈፀም ግዴታ አለባቸው።
ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-126-22-50
