ኩባንያችን ጢስ እሳት ውሃ ስራዎች ተሽከርካሪ ላይ የተጫነ ክሬን (half crane) ፤ የጭነት ተሽከርካሪ (truck tractor) ፣ ገልባጭ ተሽከርካሪ (dump truck) ፣ የኤሌክትሮ-ሜካኒካል እቃዎች (ፓምፕ እና ጄኔሬተር) ፣ ኤችዲፒ የብየዳ ማሽን ጄኔሬተሩን ጨምሮ እንዲሁም አንቲ ቫይረስ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
ኩባንያችን ጢስ እሳት ውሃ ስራዎች ተሽከርካሪ ላይ የተጫነ ክሬን (half crane) ፤ የጭነት ተሽከርካሪ (truck tractor) ፣ ገልባጭ ተሽከርካሪ (dump truck) ፣ የኤሌክትሮ-ሜካኒካል እቃዎች (ፓምፕ እና ጄኔሬተር) ፣ ኤችዲፒ የብየዳ ማሽን ጄኔሬተሩን ጨምሮ እንዲሁም አንቲ ቫይረስ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
|
ተቁ |
የእቃው አይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ |
የማቅረቢያ ጊዜ |
|
ሎት 1 |
ተሽከርካሪ ላይ የተጫነ ክሬን (half crane) |
200,000.00 |
ከ60-90 ቀናት |
|
ሎት 2 |
የጭነት ተሽከርካሪ (tuck tractor) |
200,000.00 |
ከ60-90 ቀናት |
|
ሎት 3 |
ገልባጭ ተሽከርካሪ (dump truck) |
300,000.00 |
ከስቶክ |
|
ሎት 4 |
የኤሌክትሮ ሜካኒካል እቃዎች (ፓምፕ እና ጄኔሬተር) |
200,000.00 |
ከ60-90 ቀናት |
|
ሎት 5 |
HDPE የብየዳ ማሽን ጄኔሬተሩን ጨምሮ |
100,000.00 |
ከ60-90 ቀናት |
|
ሎት 6 |
አንቲ ቫይረስ |
50,000.00 |
15 ቀናት |
ስለዚህ ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራና በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ አቅራቢ ድርጅት ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን በድርጅታችን ዌብ ሳይት www.tisisat.com ማግኘት ይችላል፡፡
የተጫራቾች መመሪያ
- ተጫራቾች የዘመኑን ግብር ከፍለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የTIN ሰርተፊኬት፣ በዘርፉ ለመሰማራት የተሰጣቸውን ፈቃድ እና ተያያዥነት ያላቸውን ማስረጃዎች ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ጨረታው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛው ቀን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 9፡30 ሰዓት ባህርዳር ከተማ አባይ ማዶ ቴዲ የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ጎን በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ተጫራቾች እና ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በድርጅታችን ዌብ ሳይት www.tisisat.com ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ በሰንጠረዥ የተመለከተውን ገንዘብ በC.P.O ወይም ያለቅድመ ሁኔታ እንደተጠየቀ ለገዥ የሚከፈል (unconditional Bank Guarantee) ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያወጡት ወጪ በተጫራቹ የሚሸፈን ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያቸውን እና ቴክኒካል ሰነዳቸውን ለየብቻ በተለያየ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ተጫራች ድርጅቶች ለሚያቀርቡት ዋጋ ለእያንዳንዱ እቃ ነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ በትክክል ሞልተው በግልፅ ማስቀመጥ አለባቸው
- ይህ ጨረታ በኩባንያችን የግዥ መመሪያ ነሐሴ /2013/ መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
- ኩባንያው በጨረታ ሰነዱ ላይ ከተገለፀው መጠን 20% ቢጨምር ወይም ቢቀንስ የጨረታ አሸናፊው ውል የመያዝ ግዴታ ይኖርበታል።
- የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ በጽሁፍ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ 05 ቀናት ውስጥ የጠቅላላ ዋጋውን 10% የውል ማስከበሪያ ያለቅድመ ሁኔታ ለገዥ የሚከፈል (unconditional Bank Guarantee) በማሰራት ውል የመያዝ ግዴታ ይኖርበታል፡፡
- የማቅረቢያ ጊዜ ከላይ በሰንጠረዡ ላይ በተገለፀው መሠረት መሆን አለበት። የአቅራቢዎች ዋጋ ቢያንስ ለ90 ቀናት ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ፀንቶ መቆየት አለበት፡፡
- ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ በዚህ ጨረታ አይገደድም ወይም ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ዕቃው ወይም አገልግሎቱ የሚቀርብበት ቦታ ባህር ዳር ከተማ የኩባንያው ጽ/ቤት መሆን አለበት፡፡
- ማሳሰቢያ፡- እንደ ኩባንያችን ፍላጎት ውድድሩ በሎት ወይም በእያንዳንዱ እቃ ነጠላ ዋጋ መሠረት ሊሆን ይችላል፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥራችን 058-220-48-26/ 058-320-25-48/በፋክስ ቁጥራችን 058 220 48-30 መጠየቅ ይችላሉ።
ጢስ እሳት ውሃ ስራዎች ኃ/የተ/የግ/ማህበር
