አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 15 ቁጥር 2 ላፍቶ ሁለገብ ገበያ ማዕከል ያስገነባቸውን የአትክልት፤ የፍራፍሬ ፣ የጥራጥሬ እና የሰብል መሸጫ አገልግሎት ሱቅና መጋዘን መስፈርቱን አሟልተው ለሚገኙ ድርጅቶች ንግድ ቢሮ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በአገልግሎት ክፍያ ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታው ዓይነት
የሱቅ እና የመጋዘን ኪራይ አገልግሎት
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 15 ቁጥር 2 ላፍቶ ሁለገብ ገበያ ማዕከል ያስገነባቸውን የአትክልት፤ የፍራፍሬ ፣ የጥራጥሬ እና የሰብል መሸጫ አገልግሎት ሱቅና መጋዘን መስፈርቱን አሟልተው ለሚገኙ ድርጅቶች ንግድ ቢሮ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በአገልግሎት ክፍያ ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡
- ተጫራቾችች አምራች ለመሆናቸው በስማቸው የተመዘገበ ህጋዊ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ ያላቸው ወይም በሰነዶች ማረጋገጫ የተመዘገበ ህጋዊ የመሬት ኪራይ ውል ማረጋገጫ ሰነድ ያላቸው ወይም በኢንቨስትመንት መሬት ወስደው ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ሰነድ በዘርፍ በመለየት በአትክልትና ፍራፍሬ እና በጥራጥሬ ሰብል ላይ ለይተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፤
- የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) ወይም በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ስም ሲፒኦ (ጋራንትድ ቦንድ) በማሰራት ማስያዝ የሚችሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያው ዋስትና ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ከመጨረሻው ቀን በኋላ ለተጨማሪ 90 ቀናት ፀንቶ ይቆያል፡፡
- ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ 1000 (አንድ ሺህ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ከመስሪያ ቤቱ አድራሻ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ደጃች ውቤ 1888 ህንጻ 8ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 803 መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳባቸውን ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው ቢሮው በሰጣችሁ ፎርማት ላይ በመሙላት የድርጅታችሁን ስም፣ የኃላፊ ስምና ፊርማ በማህተም አስደግፋችሁ ሙሉ አድራሻችሁን በመግለጽ፤
- ፋይናንሻል አንድ ኦሪጂናል እና ፋይናንሻል አንድ ኮፒ
- ቴክኒካል አንድ ኦሪጂናል እና ቴክኒካል አንድ ኮፒ በማድረግ በሰም በታሸገ በተለያየ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባችኋል፡፡
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ከሰኞ እስከ አርብ ከ2፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ ንግድ ቢሮ የግዢ ዳሬክቶሬት 8ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር -803 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣ በ11ኛው ቀን ይከፈታል ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያን ቀን ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡- 0118126179/0111703024 በመደወል መረጃ መጠየቅ ይቻላል፡፡
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ደጃች ውቤ 1888 ህንጻ 8ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 803
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የንግድ ቢሮ
