ለፐብሊክ ሠርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ነገሮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/2018
ለፐብሊክ ሠርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚውል
- ሎት 1 ልዩ ሀገር አቋራጭ ወኪል
- ሎት 2 የአገልግሎታችን አውቶቢሶች የወለል፣ የወንበር እና ውስጣዊ ግድግዳ ጥገና አገልግሎት
- ሎት 3 ስማርት ስክሪን ዲስፕለይ (smart screen Display)
- ሎት 4 የጥበቃ አገልግሎት
- ሎት 5 የተለያዩ ፕሪንተሮችና ፎቶ ኮፒ ማሽኖች ጥገና
- ሎት 6 የአውቶቢሶች የተላላጡ ክፍሎች ቀለም ለመቀባት
- ሎት 7 የሀገር አቋራጭ ባስ ኢ-ትኬቲንግ ሲስተም
- ሎት 8 የታሸገ ውሃ ባለ 330 ሚሊ
- ሎት 9 ደረቅ ኬክ ባለ 80 ግራም
- ሎት 10 ዩቶንግ ባስ ZK6122H9 መለዋወጫ ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
- ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ቀናት ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ ከድርጅቱ ቢሮ ቁጥር 28 በመምጣት መግዛት ይችላሉ።
- ከሎት 1 እስከ ሎት 10 ተጫራቶች ህጋዊ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት የምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፊኬት እንዲሁም የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ኮፒ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማያያዝ ይኖርባቸዋል።
- ሎት 1 እና ሎት 10 ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የጨረታ ሠነድ ቴክኒካልና ፋይናንሺያል ፖስታ ኮፒ እና ኦርጅናል ለየብቻ በማዘጋጀትና በኢንቨሎፕ በማሸግ ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 28 በተቀመጠ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ /Bid Bond/ በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ባልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 የስራ ቀናት ቆይቶ በ15ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 28 ይከፈታል የመክፈቻው ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም በበዓል ላይ ከዋለ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ቦታ እና ሰዓት ይከፈታል።
- አገልግሎታችን ጨረታውን በከፊልም ይሁን ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ከሜክሲኮ ወደ ልደታ ቤተክርስቲያን የሚወስደው መንገድ ላይ ፖሊስ ሆስፒታል ፊት ለፊት ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ:- ስልክ 011-5-50-45-64
ፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት
