Tender Detail

Tender Details


በአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በተለያዩ ጊዜያት የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት ባለመፈጸሙ ምክንያት እና በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስና የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ሞባይሎች ፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችና ጌጣጌጥ እና አካላት ፣ አልባሳት ጫማዎች ፣ የብር ጌጣጌጥ እና ሌሎች ዕቃዎች ባሉበት ሁኔታ በሃራጅ ጨረታ እና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።


 

ጨረታ ማስታወቂያ

 

በጉምሩከ ኮሚሽን የአ/ ኤርፖርት ጉምሩክ //ቤት ልዩ ልዩ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ እና በሃራጅ ጨረታ ቁጥር 01/2018 02/2018 03/2018 እና 04/2018 የጨረታ ማስታወቂያ

በአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ //ቤት በተለያዩ ያት የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት ባለመፈጸሙ ምክንያት እና በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስና የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ሞባይሎች የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችና ጌጣጌጥ እና አካላት አልባሳት ጫማዎች የብር ጌጣጌጥ እና ሌሎች ዕቃዎች ባሉበት ሁኔታ በሃራጅ ጨረታ እና በግልጽ ጨረታ ቁጥር 01/2018 በቀን 17/11/2017 . ጨረታ ቁጥር 02/2018 በቀን 21/11/2017 . ጨረታ ቁጥር 03/2018 በቀን 24/11/2017 . እና ጨረታ ቁጥር 04/2018 በቀን 28/11/2017 . በመሆኑ የቀጣይ 2018 በጀት ዓመት ዕቅድ በተፈለገው መጠን ለማሳካት ለሁሉም ተደራሽነት ባለው መልኩ በጋዜጣ ማስታወቂያ እንዲወጣልን እየጠየቅን ዝርዝር መረጃ ከዚህ በታች በተራ ቁጥር 1-14 እንገልፃለን፡፡

በመሆኑም

  1. በቅ//ቤቱ ለሚካሄደው ጨረታ ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ሰርተፊኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ማንኛውም የግልጽ ጨረታ ተጫራች ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ የጨረታውን ሰነድ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ዐርብ 200-600 ከሰዓት በኋላ 700-1100 እንዲሁም ቅዳሜ ጥዋት 200-600 ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመፈል ከአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ //ቤት ገርጂ ጉምሩክ መጋዘን ቅጥር ግቢ የውርስ ዕቃዎች አወጋገድ ቡድን በመምጣት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላል፡፡
  3. በግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ዋስትና (CPO) CUSTOMS COMMISSON ADDIS ABABA AIRPORT CUSTOM BRANCH OFFICE ስም ማሰራት ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች የዕቃዎቹን ናሙና በአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ካርጎ መጋዘን እና ገርጂ መጋዘን እስከ ሐምሌ 17/2017 /ም፣ ሐምሌ 21/2017 ሐምሌ 24/2017 እና ሐምሌ 28/2017 . ከቀኑ 800 ተዘግቶ በዛው ቀን 815 የሚከፈት ይሆናል፡፡
  5. በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች ለጨረታው የሚሰጡትን ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዘው በቀረቡት ቅጾች መሠረት ለመረጡት የዕቃዎች ኮድ የተሰጠ ዋጋ፣ የተጫራቾች ስም፣ አድራሻ፣ ፊርማና የጨረታ ማስከበሪያ .. (CPO) እና ከላይ በተ. 1 የተገለጹትን ሰነዶች ኮፒ በታሸገ ኢንቨሎፕ ላይ በመፈረም አዲስ አበባ ኤርፖርት ///ቤት ገርጂ የውርስ ዕቃዎች አወጋገድ ቡድን ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሰነዱ የሰጠውን መግዣ ዋጋና መግለጫ መለወጥና ማሻሻል አይችልም
  7. ማንኛውም ተጫራች የሰጠውን የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ግምገማ ተጠናቆ የጨረታው ውጤት እስከሚታወቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል
  8. የጨረታው አሸናፊዎች ጨረታውን ስለማሸነፋቸው ከተገለፀበት ጊዜ ጀምሮ 05 (አምስት) ቀናት ውስጥ ያሸነፉትን ዕቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ ዕቃውን መረከብ አለባቸው፡፡
  9. ከላይ በተ/ 8 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ፍያውን ገቢ ያላደረገ እና ንብረቱን ተረክቦ ያልወሰደ ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት .. (CPO) ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡
  10. በተራ ቁጥር 01 - 09 የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ በተጨማሪም በሃራጅ ጨረታ ቁጥር 01/2018 በቀን 17/11/2017 . ጨረታ ቁጥር 02/2018 በቀን 21/11/2017 .ም፤ ጨረታ ቁጥር 03/2018 በቀን 24/11/2017 . እና ጨረታ ቁጥር 04/2018 በቀን 28/11/2017 . ዋቱ 400 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የምናካሄድ መሆኑን በዚሁ አጋጣሚ እያሳወቅን፤ የዕቃዎችን ናሙና በአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ //ቤት ገርጂ እና ካርጎ ውርስ መጋዘን በመገኘት መመልከት ይቻላል፡፡
  11. በሃራጅ ጨረታ የሚወዳደሩ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000.00 /መቶ ሺህ/ ለየዘርፉ CUSTOMS COMMISSION ADDIS ABABA AIRPORT CUSTOM BRANCH OFFICE ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል፣
  12. ለጨረታ የቀረቡት የዕቃዎች ዋጋ ከቫት በፊት የተሰጠ መሆኑ እናሳውቃለን፡፡
  13. ለጨረታ የቀረቡት ዕቃዎች በተናጠል ሳይሆን ለጨረታው ሰነዱ በተሰጠ ኮድ ቁጥር ብቻ የሚሸጥ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
  14. //ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር ቦሌ ኤርፖርት 0116684537 እና 0116684193 ይጠይቁ

 

በጉምሩክ ኮሚሽን / ርፖርት ጉምሩክ //ቤት

 

Save Tender