የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሰሜን ምስራቅ አዲስ አበባ ዲስትሪክት፤ ደቡብ ምዕራብ አዲስ አበባ ዲስትሪክት እና ደብረ-ብርሃን ዲስትሪክት ግዴታቸውን ከማይወጡ የካፒታል ዕቃ ተከራዮች የሚረከባቸውን ማሽኖች ተረክቦ የሚያስቀምጥበት መጋዘን በጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል፡፡
የክርስቲያናዊ ወንድማማች ቤተ ክርስቲያን የህፃናት እርዳታ ድርጅት
ድጋሚ የወጣ የመጋዘን ኪራይ ጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሰሜን ምስራቅ አዲስ አበባ ዲስትሪክት፤ ደቡብ ምዕራብ አዲስ አበባ ዲስትሪክት እና ደብረ-ብርሃን ዲስትሪክት ግዴታቸውን ከማይወጡ የካፒታል ዕቃ ተከራዮች የሚረከባቸውን ማሽኖች ተረክቦ የሚያስቀምጥበት መጋዘን በጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በአዲስ አበባና በሸገር ከተሞች ውስጥ የመጋዘን ኪራይ አገልግሎት የምትሰጡ ግለሰቦችና ድርጅቶች የምታከራዩበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሐምሌ 23 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሰሜን ምስራቅ አዲስ አበባ ዲስትሪክት 2ኛ ወለል ላይ በሚገኘውና ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ትችላላችሁ፡፡ ጨረታው ሐምሌ 24 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
ለኪራይ የሚቀርቡ መጋዘኖች፡-
- የመጋዘኑ ስፋት ከ1500 ካ.ሜ ያላነሰ ፤ ቁመቱ ቢያንስ 6 ሜትርና ሰፊ ግቢ ያለው መሆን አለበት፤
- ግንባታቸው ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቀ መሆን ይኖርባቸዋል፤
- የመጋዘኑ በር ዕቃ የጫነ መኪና ፤ ዕቃ የሚጭንና የሚያወርድ ማሽን ገብቶ ያለምንም የቦታ ጥበት ማንቀሳቀስ የሚያስችል መሆን ይኖርበታል፤
- ከዋና መንገድ (ከመሀል ከተማ) ብዙ ያልራቀና መሠረተ ልማቱ የተሟላ መሆን አለበት፤
- ውሃ ፤ መብራት እና የጥበቃ መኖሪያ ቤት ቢኖረው ተመራጭ ይሆናል፤
- የኪራይ ዘመኑ ቢያንስ 3 ዓመትና ከዚያ በላይ መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታና የታደሰ የግብር ከፋይ ማረጋገጫ ሰነድ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፤
- ጨረታውን ያሸነፈ ጨረታውን ማሸነፉ ከተነገረው ቀን ጀምሮ በአንድ ሣምንት ጊዜ ውስጥ አስፈላጊውን ሁሉ አሟልቶ የውል ስምምነት ተፈራርሞ መጋዘኑን ማስረከብ አለበት፡፡
- ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉም ሆነ በከፊል ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- ካዛንቺስ ሾንጌ ህንጻ 2ኛ ፎቅ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሰሜን ምስራቅ አዲስ አበባ ዲስትሪክት
