ኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ለተለያዩ ፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚውል ኤክስካቬተር ከነ ጃካመሩ በዘርፉ የተሰማሩ አቅራቢዎችን በግልጽ ጨረታ በማወዳዳር መግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
ኮርፖሬሽናችን ለተለያዩ ፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚውል ኤክስካቬተር ከነ ጃካመሩ በዘርፉ የተሰማሩ አቅራቢዎችን በግልጽ ጨረታ በማወዳዳር መግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም ከዚህ በታች ኮርፖሬሽናችን ያስቀመጣቸውን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተወዳዳሪ ድርጅቶች በጨረታው መወዳዳር ይችላሉ።
|
ተ.ቁ |
የእቃው ዓይነት |
መለያ |
መለያ |
ብዛት |
ምርመራ |
|
1 |
ሀይድሮሊክ ቸን ኤክስካቬተር |
በጨረታ ሰነዱ ላይ ተያይዟል |
ቁጥር |
02 |
|
|
2 |
ጃካመር |
በጨረታ ሰነዱ ላይ ተያይዟል |
ቁጥር |
02 |
|
- ተወዳዳሪዎች የዘመኑን ግብር ከፍለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የTIN ሰርተፊኬት፣ እንዲሁም በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የታክስ ክሊራንስ ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የተሰጠ ደብዳቤ እና ሌሎች ቴክኒካል ሰነዶችን ኮፒ (ቅጅ) እና ኦርጅናል (ዋና) በማለት ለየብቻ በፖስታ በማድረግ እንዲሁም የፋይናንሻል (የዋጋ) መሙያ ሰነዳቸውን ኮፒ (ቅጅ) እና ኦርጅናል (ዋና) በማለትና ለየብቻ እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያውን ለብቻ በማድረግ በአንድ በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 20 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የመወዳዳሪያ ሰነዳቸውን ባህር ዳር ከተማ ከሚገኘው ዋና መ/ቤታችን የግዥ ዳይሬክቶሬት ክፍል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ጨረታው በ20ኛው ቀን ከቀኑ 9፡00 ታሽጎ በዚሁ እለት 9፡30 ይከፈታል። ይሁን እንጂ 20ኛው የመክፈቻ ቀን ከኮርፖሬሽናችን የሥራ ሰዓት ውጭ ከሆነ እና የመንግስት ካላንደር የሚዘጋው ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
- የሚቀርበው የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ሕጋዊ የድርጅቱ ተወካይ ስም፣ ፊርማና ማህተም ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ አዲስ አበባ የኮርፖሬሽናችን ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ድረስ የማጓጓዝ እና ሌሎች ከእቃዎች ጋር የተያያዙ ማንኛውም ወጪዎች ተጫራቹ የሚሸፍን ይሆናል።
- በዚህ ጨረታ የሚሰጠው የመወዳደሪያ ዋጋ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ60 (ስልሳ) ተከታታይ ቀናት የጸና ይሆናል።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሽህ ብር) የያዘ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ በኮርፖሬሽናችን ስም ማለትም ኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን (Hibir Construction Corporation) በሚል የተሰራ እና ጨረታው ከሚከፈትበት ቀን ጀምሮ ለ90 (ዘጠና) ቀናት ጸንቶ የሚቆይ ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች በጨረታው ማሸነፋቸው በደብዳቤ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 05 (አምስት) ተከታታይ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በኮርፖሬሽናችን ስም የተሰራ የባንክ ዋስትና (የውል ማስከበሪያ ዋስትና) ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ከአቅም በላይ የሆኑ ችግሮች ሲከሰቱ በሁለቱ ወገን /በሻጭ እና በገዥ የጋራ ውይይት ችግሩ ይፈታል። በጋራ ችግሮችን ለመፍታት ካልተቻለ በሚመለከተው ፍርድ ቤት ሁለቱም ወገን ቀርበው በሚወሰነው ውሳኔ የሚፈጠረው አለመግባባት ይፈታል፡፡
- ይህ የጨረታ ግዥ ሥርዓት እና መመሪያ የጨረታው የውል አካል ሆኖ ይወሰዳል።
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቶች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም።
- በጨረታው ለተገለጸው ማሽን ዝርዝር የጨረታ ሰነድ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመከፈል ከኮርፖሬሽናችን ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 23 ቀርበው መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታውን ለማሸነፍ እንዲረዱት ለማንኛውም የኮርፖሬሽኑ ኃላፊ ወይም ሠራተኞች መደለያ የሰጠ ተጫራች አግባብ ባለው የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ድንጋጌ መሠረት መጠየቁ እንደጠበቀ ሆኖ ከጨረታው እንደሚሰረዝ ፣ አሸንፎ ውል ቢዋዋልም ውሉ ይሰረዛል።
ኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን
