ቦሌ ማተሚያ ኃ.የተ.የግ.ማህበር የተለያየ መጠን ያላቸው ፖስታዎች/ ኤንቨሎፕ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የሀገር ውስጥ የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
ቦሌ ማተሚያ ኃ.የተ.የግ.ማህበር ሎት 1. የተለያየ መጠን ያላቸው ፖስታዎች/ ኤንቨሎፕ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ሎት 2. ቁርጥራጭ እና ግልፋፊ ወረቀቶች፣ የወረቀት ኮር፣ ፕሌቶች፣ የቀለም ቆርቆሮ ባለ አንድ እና ሁለት ኪሎ መጠን ያለው በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
-
- ተጫራቾች:- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የቫት ተመዝጋቢ የምስክር ወረቀት፣ የንግድ ሰርተፊኬት እና ሌሎችም የህጋዊነት ማረጋገጫ ሰነዶችን ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በቅድሚያ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ/ ቢሮ ቁጥር 101 በመክፈል ለዚሁ ጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ድረስ ቦሌ መንገድ ከቶታል ነዳጅ ማደያ ዝቅ ብሎ በሚገኘው ቢሮአችን መግዛት ይኖርባቸዋል፡፡
- ለሎት 1 የሚሳተፉ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የዋጋቸውን 2%፣ ለሎት 2 የሚሳተፉ ደግሞ ብር 30,000 (ሰላሳ ሺ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ /ሲፒኦ/ በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ቴክኒካል እና ፋይናንሺያል ሰነዶችን በአንድ ፖስታ አሽገው ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከግዥ ክፍል በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ያስገባሉ፡፡
- ለፖስታዎች የሚሳተፉ ተጫራቾች ሰነድ ሲገዙ ናሙናዎቹን በአይን በማየት ከሚያስገቡት ሰነድ ጋር የሚያቀርቡትን ሳምፕል አያይዘው የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡
- ለሎት 2 የሚሳተፉ ተጫራቾች በቅድሚያ ከቦታው በመምጣት የሚሸጠውን ንብረት ማየት ይችላሉ። እንደዚሁም በኪሎ/በነጠላ የሚሰጡት ዋጋ ተ.እ.ታ 15% በማካተት በግልጽ ተጽፎ መቅረብ አለበት።
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባለው 15ኛው ቀን ከረፋዱ 3፡00 ሰዓት ላይ የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በ3፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በማህበሩ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- ድርጅቱ ሌላ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡ ቦሌ መንገድ ከቶታል ነዳጅ ማደያ ዝቅ ብሎ
ቦሌ ማተሚያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
ስልክ ቁጥር ............ 01115 15 50 05/0115 51 88 72
ፋክስ ............ 0115 51 86 96
ፖ.ሳ.ቁጥር ...... 2365
ቦሌ ማተሚያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
