የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ክሐምሌ 1, 2016 እሰከ ሰኔ 30, 2017 ዓ.ም አመታዊ አዲት ለማስደረግ የውጭ ኦዲተር በሀገር ውስጥ ጨረታ በግልጽ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
በድጋሚ የወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ክሐምሌ 1, 2016 እሰከ ሰኔ 30, 2017 ዓ.ም አመታዊ አዲት ለማስደረግ የውጭ ኦዲተር በሀገር ውስጥ ጨረታ በግልጽ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት
- ተጫራቾ በጨረታው ለመወዳደር ከህጋዊ አካል ማለትም ከታወቀ የሂሳብ አያያዝ አዲት ቦርድ የተረጋገጠ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
- በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የቲን እና ቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የዘመኑ ታክስ የከፈሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ብር 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር) ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን ቴክኒካልና ፋይናንሻል ለብቻው በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት በፌዴሬሽኑ ቢሮ ቁጥር 5 ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። የጨረታ ሳጥኑ በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ይታሸጋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት በፌዴሬሽኑ ቢሮ ቁጥር 5 (መሰብሰቢያ አዳራሽ) ይከፈታል። የመክፈቻ ቀን ቅዳሜ፣ እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል።
- ተጫራቾች ጨረታውን በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመክፈል ጉርድ ሾላ በሚገኘው በፌዴሬሽኑ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 5 በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ጉርድ ሾላ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሕንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 6
ለበለጠ መረጃ፡- 0911104814/0911-41-64-83 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
ፖ.ሳ.ቁ 13336
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን
