ሞሃ የለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ አክሲዮን ማህበር ሽሮ ሜዳ በሚገኘው የድርጅቱ መጋዘን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያዩ ያገለገሉ ዕቃዎች በጨረታ በማወዳደር ባሉበት ሁኔታ መሸጥ ይፈልጋል።
ያገለገሉ ዕቃዎች የጨረታ ሠነድ የጨረታ ቁጥር - Service 0006/2017
ሞሃ የለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ አክሲዮን ማህበር ሽሮ ሜዳ በሚገኘው የድርጅቱ መጋዘን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያዩ ያገለገሉ ዕቃዎች በጨረታ በማወዳደር ባሉበት ሁኔታ መሸጥ ይፈልጋል። ስለዚህ ዕቃዎቹን መግዛት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ለዚሁ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ሸገር ዱቄትና ዳቦ ፋብሪካ ቅጥር ግቢ አዲስ በተገነባው ህንጻ ሦስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 003 በመውሰድ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
በዚሁ መሠረት፣
- ተጫራቾች ለጨረታ የቀረቡትን የተለያዩ ዓይነት ያገለገሉ ዕቃዎችን ሽሮ ሜዳ በሚገኘው የድርጅቱ መጋዘን በአካል ተገኝተው በማየት ዋጋቸውን በታሸገ ኤንቬሎፕ ከሐምሌ 22 ቀን 2017 ጀምሮ እስከ ነሐሴ 02 ቀን 2017 ዓ.ም ለ10 ቀናት እስከ ቀኑ 8:00 ሰዓት ድረስ ከላይ በተገለፀው መ/ቤት አድራሻ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ 8፡00 ላይ ተዘግቶ 8፡30 ሰዓት ላይ በዋናው መ/ቤት መገኘት በሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ፊት ይከፈታል።
- በጨረታው የሚሳተፍ ተጫራች 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡-
→ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ሸገር ዱቄትና ዳቦ ፋብሪካ ቅጥር ግቢ አዲስ በተገነባው ህንጻ 3ኛ ፎቅ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ነሐሴ 02 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ድረስ የጨረታ ሰነዱን በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማሸግና የጨረታ ሳጥን ውስጥ በማስገባት መወዳደር ይችላሉ።
ማሳሰቢያ፡-
- ሲፒኦውን በማንኛውም ባንክ በሞሃ የለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ አክሲዮን ማህበር ስም ማሰራት ይችላሉ።
- ዋጋ ሲያስቀምጡ ስርዝ ድልዝ ወይም በተመለከተው ሠንጠረዥ መሠረት በትክክልና በግልጽ የዋጋ ማቅረቢያ መሠረት ግልጽ መረጃ መስጠት ያለበት ሲሆን ነገር ግን አሻሚ የሆነ ሰነድ ቢገኝ ውድቅ ይሆናል።
ሞሓ የለስላሳ መጠጦች
