የሕዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን በስሩ ያሉትን ለተለያዩ ፓርኮች ለሶስተኛ ወገን በማስተላለፍ እንዲተዳደር ለማከራየት ይፈልጋል።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 01
የሕዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን በስሩ ያሉትን ለተለያዩ ፓርኮች ማለትም፡-
ሎት 1፡- የሕዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳዳር ኮርፖሬሽን በውስጡ የሚያስተዳድራቸው በኮሪደር ልማት የለሙ በካሳንችስ፣ መገናኛ፣ ሽሮ ሜዳ፣ ግንፍሌ፣ ሳር ቤት፣ ለቡ፣ ጀሞ፣ መካኒሳ፣ ጀርመን አደባባይ፣ 22 ማዞሪያ፣ ለም ሆቴል አካባቢ፣ ለሚ ኩራ፣ ሰሚት፣ አቦ ማዞሪያ፣ ቄራ፣ ጎሮ፣ ሂልተን አካባቢ፣ ብስራተ ገብርኤል፣ አንበሳ ጋራጅ፣ ገርጂ መብራት ኃይል አካባቢ ገርጅ ኦቪድ ሪል ስቴት አካባቢ የሚገኙ የተለያዩ ፓርኮችን ለማከራየት፣
ሎት 2፡- ኮሪያ ፓርክ ውስጥ ሁለት ሱቆችን ለማከራየት፣ አራት ኪሎ ፕላዛ ውስጥ የሚገኙ ሱቆችን ለማከራየት፣
ሎት 3፡- ሸገር ፓርክን ሙሉ ለሙሉ ለሶስተኛ ወገን በማስተላለፍ እንዲተዳደር ለማከራየት፤
ሎት 4፡- ኮልፌ ፓርክን ሙሉ ለሙሉ ለሶስተኛ ወገን በማስተላለፍ እንዲተዳደር ለማከራየት፤
ሎት 5፡- ገዳመ ኢየሱስ ፓርክን ሙሉ ለሙሉ ለሶስተኛ ወገን በማስተላለፍ እንዲተዳደር ለማከራየት፤
ሎት 6፡- ኮልፌ ፓርክን ሙሉ ለሙሉ ለሶስተኛ ወገን በማስተላለፍ እንዲተዳደር ለማከራየት፤
ሎት 7፡- ከንቲባ ወ/ጻዲቅ ፓርክን ሙሉ ለሙሉ ለሶስተኛ ወገን በማስተላለፍ እንዲተዳደር ለማከራየት፤
ሎት 8፡- አምባሳደር ፓርክን ሙሉ ለሙሉ ለሶስተኛ ወገን በማስተላለፍ እንዲተዳደር ለማከራየት፤
ሎት 9፡- ካሌብ ፓርክን ሙሉ ለሙሉ ለሶስተኛ ወገን በማስተላለፍ እንዲተዳደር ለማከራየት፤
ሎት 10:- ሚሊኒም ፓርክን ሙሉ ለሙሉ ለሶስተኛ ወገን በማስተላለፍ እንዲተዳደር ለማከራየት፤
ሎት 11፡- መለስ ፓርክን ሙሉ ለሙሉ ለሶስተኛ ወገን በማስተላለፍ እንዲተዳደር ለማከራየት፤
ሎት 12፡- አቃቂ ፓርክ ሙሉ ለሙሉ ለሶስተኛ ወገን በማስተላለፍ እንዲተዳደር ለማከራየት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በኪራይ ማስተላለፍ ይፈልጋል።
በመሆኑም የተጠቀሱትን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች ተጋብዘዋል።
- ተጫራቾች በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ፓርኮቹ ውስጥ ገብቶ ለመስራት ፍቃደኛ የሆነና የተቋማችን ጋር ውል ገብቶ በገበያ ጥናት እና የመነሻ ዋጋ መሰረት ተወዳድረው አስፈላጊውን ክፍያ የሚከፍልና በውሉ መሰረት ግዴታውን መወጣት የሚችል።
- በግቢ ያሉ ፋውንቴኖችን፣ መናፈሻዎችን ፣ የመጸዳጃ ቤቶችን ፣ የጽዳት ፣ የጥበቃ የተለያዩ ጥገናዎችን ከሌሎች ተከራዮች ጋር በመሆን ማስጠገን፣ መቆጣጠርና በአግባቡ ማስተዳደር የሚችል።
- ለሕዝብ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ተመጣጣኝ የገበያ ዋጋ ለማቅረብ ፍቃደኛ የሆነ።
- ኮርፖሬሽኑና የከተማ አስተዳደሩ በሚወጣው የሥራ ሰዓት፣ ቅዳሜ እና እሁድ፣ በዓላትን እንዲሁም ምሸትን ጨምሮ አገልግሎት መስጠት የሚችል።
- አሸናፊነት ከታወቀ በኋላና ውል ከወሰደ በኋላ በ3 ቀን ውስጥ ሥራ መጀመር የሚችል
- ስታንዳርዱን የጠበቀ እና የኮሪደር ልማቱን የሚመጥን እቃዎችን ይዞ መግባት የሚችል።
- ከተቻለ በሬስቶራንት ፣ በካፌ እና ሕዝብ መዝናኛ ፓርክ ላይ ልምድ ያለውና መረጃ ማቅረብ የሚችል።
- ተጫራቾች ለሎት አንድ እና ሁለት 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲፒኦ ወይም ባንክ ጋራንቲ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሕዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን ስም ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 500 /አምስት መቶ ብር/ ቦሌ ማተሚያ ፊት ለፊት ገባ ብሎ የድሮው ፒኮክ መናፈሻ ጊቢ ውስጥ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አስር ተከታታይ የሥራ ቀን ከጠዋት 2፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ በመቅረብ መግዛት ይቻላል።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ፋይናንሻል ዶክመንት እና ቴክኒካል ዶክመንት ለየብቻ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሳጥኑ እስከሚታሸግበት ከ10ኛው ተከታታይ የሥራ ቀን በኋላ ከአለው 11ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ድረስ ለዚህ ተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ሳጥኑ ታሽጎ በዚያው ቀን ጠዋት 4፡30 ቦሌ ማተሚያ ፊት ለፊት ገባ ብሎ የድሮው ፒኮክ መናፈሻ ጊቢ በግዥና ንብረት ዳይሬክትሬት ቢሮ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል።
- የጨረታ መክፈቻው ቀን ቅዳሜና እሁድ ላይ የሚውል ከሆነ በቀጣዩ ሰኞ በተጠቀሰው ሰዓት ተዘግቶ የሚከፈት ይሆናል።
- ዘግይቶ የደረሰ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
- ኮርፖሬሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0703614456/0977246014 ደውለው መጠየቅ ይቻላል።
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሕዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን
