አንፆ/ገ/ወ/ዘብ ጽ/ቤት ግዥ ቡድን አገልግሎት ለሚመለከታቸው ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል የመኪና ጎማዎች፤ የመኪና መለዋወጭ እቃዎች /Spare Parts/፤ የማሽነሪዎች ጥገና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የአንፆ/ገ/ወ/ዘብ ጽ/ቤት ግዥ ቡድን አገልግሎት ለሚመለከታቸው ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል
ሎት1 የመኪና ጎማዎች
ሎት2 የመኪና መለዋወጭ እቃዎች /Spare Parts/
ሎት3 የማሽነሪዎች ጥገና
ከላይ የተዘረዘሩት እቃዎች በየዘርፉ ንግድ ፍቃዳቸውን በሚጋብዛቸው መሠረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታው ለመሣተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች በሙሉ ሕጋዊና በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድና ከመንግስት የሚጠበቅባቸውን የዘመኑ ግብር የከፈሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር አርጅናልና ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ።
- በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ 50 /አምሳ ብር/ በመክፈል ከ25/11/2017 እስከ 9/12/2017 ዓ.ም ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 1 ድረስ በመምጣት መግዛት ይችላሉ።
- የጨረታ ሰነዱ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በፖስታው እና ዋጋው መሙያው ላይ የድርጅቱን ማህተምና ፈርማ በግልጽ በማስቀመጥ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይቻላል።
- የጨረታ ሳጥኑ 10/12/2017 ዓ.ም 4፡01 ሰዓት ላይ ታሽጐ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ 10/12/2017 ዓ.ም ቀን 4፡30 ላይ ይከፈታል፣
- ተጫራቾች የጨረታው ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንከ ከተፈቀደላቸው የታወቁ ባንኮች የሚሰጥ እንደ ተጫራቾቹ ምርጫ የጠቅላላ ዋጋውን 1% በጥሬ ገንዘብ /CPO/ ወይንም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና በፖስታው ውስጥ አሽጐ ማስገባት ይኖርበታል፣
- ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለተሸናፊዎች አሸናፊ ውል ከፈጸመ በኋላ የሚመለስ ሲሆን ለአሸናፊው ድርጅት ውል ፈጽሞ 10% የውል ማስከበሪያ እንዳስያዘ የጨረታ ማስከበሪያው ይመለስለታል።
- አሸናፊው ተጫራች ማሸነፋ ከተገለጸለት ከ5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ውል መግባት ይጠበቅበታል። ያስያዘው 10% የውል ማስከበሪያ ያሸነፈበትን እቃ ሙሉ በሙሉ እንፆ/ገ/ወ/ግ/ን/አስ/ደር ቡድን መካዝን ካስረከበ በኋላ ከ30 ቀናት በኋላ ይመለስለታል።
- በሁሉም ሎቶች የሚወዳደሩ ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
- መ/ቤቱ የሚገዛውን እቃ ብዛት 20% የመጨመርና የመቀነስ መብት አለው።
- መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብት አለው፡፡
- ተጨማሪ መረጃዎችንና የጨረታ ሰነድ በአንፆ/ገ/ወ/ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 06 ማግኘት ይችላሉ።
- ውድድሩ የሚደረገው በእያንዳንዱ ሎት በጥቅል ድምር ዋጋ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 033 444 0562/033 444 00 11 ይጠይቁ
ማሳሰቢያ፡- የመክፈቻው ቀን በዓል ላይ ከዋለ በሚቀጥለው ሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
የአንፃኪያ ገምዛ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
