የሲዳማ ብ/ክ/መ/ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች በሎት የተገለጸውን ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የሲዳማ ብ/ክ/መ/ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች በሎት የተገለጸውን ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ሎት 1 የኤሌከትሮኒክስ ግዥ፣
ሎት 2 የፈርኒቸር ግዥ፣
ሎት 3 የመጋረጃ እና ምንጣፍ ግዥ፣
በመሆኑም ተጫራቾች፡-
- የዘመኑን ግብር የከፈሉና በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ሲሆን የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የተመዝጋቢነት ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) እየከፈሉ ከመ/ቤቱ ግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋቸውን 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር ብቻ) በጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፣ ጨረታው የቴክኒካል እና የፋይናንሻል ሰነድ አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ መቅረብ አለበት፡፡ ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በታሸገ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ እስከ 15ተኛው ቀን 8:00 ሰዓት ድረስ በድርጅቱ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ እለቱ የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ8፡30 ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሂሳብ ላይ ስማቸውን፣ ፊርማቸውን፣ አድራሻቸውን እና ስልክ ቁጥራቸውን ማስፈር አለባቸው፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡- 046-2-21-70-14 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የመ/ቤቱ አድራሻ ከሀዋሳ ገብርዔል ቤ/ክርስትያን ፊት ለፊት ነው፡፡
የሲዳማ ብ/ክ/መ/ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ
