የአዳማ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የፍታብሔር ጉዳይ ችሎት በአፈፃፀም ክርክር ጉዳይ አስመልክቶ በአዳማ ከተማ ሉጎ ክፍለ ከተማ ድሬ ነገያ ወረዳ ውስጥ የሚገኘውን ቦታ በጨረታ እንዲሸጥ ወስኗል። ስለሆነም መግዛት የምትፈልጉ ሰዎች በዚህ ጨረታ ላይ እንድትሳተፉ ይጋብዛል።
የጨረታ ማስታወቂያ
በፍርድ ባለመብት ሰላም ባልቻ እና በፍርድ ባለዕዳ ኪያ ለገሰ መካከል ያለውን የአፈፃፀም ክርክር አስመልክቶ በአዳማ ከተማ ሉጎ ክፍለ ከተማ ድሬ ነገያ ወረዳ ውስጥ በፍርድ ባለዕዳ ስም የተመዘገበው የካርድ ቁጥሩ OR001032801010 የጨረታ መነሻ ግምት ብር 6,067,962.41% (ስድስት ሚሊየን ስልሳ ሰባት ሺህ ዘጠኝ መቶ ስልሳ ሁለት 41% ሳንቲም) ስለሆነ መግዛት የምትፈልጉ ሰዎች ከጨረታው ግምት ውስጥ 1/4 ሲፒኦ በማስያዝ ግልጽ በሆነ ጨረታ በፍ/ስ/ስ/ አንቀጽ 423 (1 እና 2)፣ 425 (1 እና 2) እና 426 መሰረት ከ3፡00 ሰዓት እስከ 6፡30 ድረስ ቤቱ በሚገኝበት ቦታ የጨረታው ኮሚቴ መግዛት የምትፈልጉ ሰዎችን አወዳድሮ የሚሸጥ መሆኑን ይገልፃል፡፡ በመሆኑም መግዛት የምትፈልጉ ቀርባችሁ መግዛት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
በአዲስ ዘመን ጋዜጣ የወጣው የጨረታ ማስታወቂያ በአየር ላይ የሚቆየው ከቀን 28/11/2017 ጀምሮ እስከ 28/12/2017 ለአንድ () ወር/ለተከታታይ 30 ቀናት ይሆናል፡፡
- መግዛት የምትፈልጉ ሰዎች መነሻ ዋጋ የጨረታ ግምት ብር 6,067,962.41% (ስድሰት ሚሊየን ስልሳ ሰባት ሺህ ዘጠኝ መቶ ስልሳ ሁለት 41% ሳንቲም) 1/4 ሲፒኦ በባንክ ማስያዛችሁን ማስረጃ /ስሊፕ/ ማቅረብ ይኖርባችኋል፡፡
በአዳማ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የፍታብሔር ጉዳይ ችሎት
