በሲዳማ ክልላዊ መንግስት በሀዋሳ ከተማ የአዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል ለ2018 በጀት ዓመት የሚሆን ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በሲዳማ ክልላዊ መንግስት በሀዋሳ ከተማ የአዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል ለ2018 በጀት ዓመት የሚሆን ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ሎት 1. የህዝብ መድኃኒት ቤት መድኃኒት ግዥ
ሎት 2. አዳሬ ግቢ መድኃኒት ግዥ
ሎት 3. ኤሌክትሪክ ዕቃዎች ግዥ
ሎት 4. ውሃ ዕቃዎች ግዥ
ሎት 5. ህንፃ መሳሪያ ግዥ
ሎት 6. ፅህፈት መሳሪያ ግዥ
ሎት 7. ጽዳት ዕቃዎች ግዥ
ሎት 8. ላቦራቶር ሪኤጀንት ግዥ
ሎት 9. ህትመት ግዥ
ሎት 10. የህክምና መገልገያ መሣሪያዎች ግዥ
ተጫራቾች
- ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያለው
- የዘመኑን የ2017 ዓ/ም ግብር የከፈሉ፣
- እንደ አስፈላጊነቱ የቫት ተመዝጋቢ የሆነ፣
- በመስኩ የንግድ ሥራ የተሰማሩ
- የጨረታ ማስከበሪያ በሆስፒታሉ ስም የተሠራ CPO 10,000 (አስር ሺህ ብር) ማስያዝ የሚችሉ፤
- የጨረታ ሰነዱ አዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል ግዥ ክፍል በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነድ አንድ ኦርጅናል ሁለት ኮፒ ለየብቻ ፋይናንሻል እና ቴክኒካል በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በድምሩ 6 ፖስታ ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ እንዲያስገቡ ሆኖ በ15ኛው ቀን ከረፋዱ 6፡00 ሰዓት ላይ የጨረታ ማስገቢያ ሳጥን ይታሸግና ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
ይህ ቀን ቅዳሜ ወይም እሁድ እንዲሁም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው በሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
ማሳሰቢያ፡-
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙ ጨረታው ተከፍቶ ውሳኔ ይሰጣል፡፡ መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው።
- ፋይናንሻል ሠነድ ከሆስፒታሉ የተዘጋጀው ላይ ብቻ ዋጋ መሙላት ይገባል።
- በፋይናንሻል ሠነድ ላይ የዋጋ መሙያን መቀየርም ሆነ ከተጠየቀው ይዘት ውጪ መለኪያ በመቀየር ዋጋ ሞልቶ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- ተጨማሪ መረጃ የስልክ ቁጥር 0462122370
በሲዳማ ክልላዊ መንግስት በሀዋሳ ከተማ የአዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል
