Tender Detail

Tender Details


በአዲስ ከተማ ጤና ጣቢያ ለ2018 በጀት አመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ነገሮች በጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።


 

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 001

 

በአዲስ ከተማ ጤና ጣቢያ 2018 በጀት አመት በአዲስ ዘመን በጋዜጣ በወጣው ግልጽ ጨረታ ለተጫራቾች የተዘጋጀ አገልግሎት ግዥ Lot 1 ጀነሬተር service ጥገና (ሜንቴናንስ) አወዳድሮ ለአንድ አመት ለማስጠገን ይፈልጋል፡፡ እዲሁም Lot 2 የጽህፈት መሳሪያ Lot 3 የጽዳት እቃ Lot 4 ኤሌክትሮኒክስ እና የጥገና እቃ Lot 5 ህትመት Lot 6 ደንብ ልብስ እና ስፌት Lot 7 የኮምፒውተር ጥገና Lot 8 ቋሚ እቃ Lot 9 መድሃኒት እና የህምና እቃዎች አወዳድሮ ለመግዛት እንዲሁም Lot 10 የሽንት ቤት ቆሻሻ መጸዳጃ ማስወገድ አገልግሎት ለአንድ አመት በጨረታ አወዳድሮ ለማስወገድ ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ በመስኩ የተሰማራችሁ አቅራቢዎች

  1. በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር
  3. በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገበ
  4. የተጨማሪ እሴት ታክስ /vat/ ሰርተፍኬት ወይም TOT 2%
  5. በመድሀኒት ላይ የምትወዳደሩ ተጫራቾች ከኢትዮጵያ ምግብና መድህኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ላይሰንስ ሊኖር ይገባል፡፡
  6. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ግዜ ጀምሮ ተመላሽ የሚሆን የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ lot1 ጀነሬተር service 2% (3000) lot2 የጽፈት መሳሪያ 2% (4000) lot3 የጽዳት እቃ 2% (6000) lot4 ኤሌክትሮኒ የጥገና እቃ 2% (3000) lot5 ህትመት 2% (5000) lot6 ደንብ ልብስና ስፌት 2% (4000) lot7 የኮምፒውተር ጥገና 2% (2000) lot8 ቋሚ እቃ 2% (10000) Lot9 መድሃኒት እና የህክምና እቃዎች 2% (10000) Lot10 የሽንት ቤት ቆሻሻ መጸዳጃ ማስወገድ አገልግሎት 2% (2000) ብቻ በባንክ በተረጋገጠ /ሲፒኦ/ ከጨረታ ሰነድ ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ለዚሁ ጨረታ የተዘጋጀውን ዝርዝር ጉዳዮች እና የተጫራቾችን መመሪያ የያዘ ሰነድ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ረታ ሰነድ ብር 200 /ሁለት መቶ/ ብር በመግዛት መውሰድ ይችላሉ፡፡
  8. ጨረታው መጀመሪያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 የስራ ቅናት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እስከ 11:30 ድረስ ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል ጨረታው የሚዘጋው 11ኛው ቀን ከጠዋቱ 2:30 ታሽጎ 300 ላይ ተጫራቶች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  9. አሸናፊው ድርጅት ውል በተፈራረሙበት 15 ቀን ውስጥ እቃውን ያቀርባል፡፡
  10. አሸናፊ ሆኖ የተመረጠው ድርጅት በአካል በመቅረብ ስራውን ማከናወን አለበት
  11. ጨረታው ከተከፈተ ተጫራ ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ ወይም ከጨረታው እራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
  12. ተጫራቾች የዋጋ ዝርዝራቸውን በገዙት ረታ ሰነድ ላይ ብቻ ሞልተው እና በእያንዳንዱ ገጽ ላይ ማህተም በማድረግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  13. የጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብም ሆነ ድርጅት ውል በሚያዝበት ወቅት ያሸነፈበትን የሽያጭ ቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዛዝ (cpo) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  14. ተጫራቾቾ በገዙት ሰነድ መሰረት የሚወዳደሩበትን ዋጋ 15% vat ያካተተ መሆኑን ወይም አለመሆኑን መጠቀስ ይኖርበታል፡፡ ካልተጠቀሰ እንደተካተተ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
  15. ኦርጅናል ሰነድ ከሙሉ ሰነድ ጋር እና ኮፒውን ሰነድ ለየብቻ ተደርጎ በማያያዝ ማስገባት ይኖርባቸዋል እንዲሁም የድርጅቱ ማህተም እያንዳንዱ ሰነዶች ላይ መደረግ አለበት፡፡
  16. /ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
  17. ማንኛውም ተጫራች መደበኛ የጨረታ ሰነዱን የሚሞሉ ፍሎችን በአግባቡ ሞልቶ ተመላሽ ያላደረገ አቅራቢ ቅድመ ምርመራ ጨረታ ላይ ውድቅ ይደረጋል።
  18. የጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጀ ልዩ አስተያየት የሚደረገው በሚያመርቱት ምርት ብቻ ሆኖ ከተደራጁበት ተቋም በሚያቀርቡት ደብዳቤ ይሆናል፡፡

ተጨማሪ መረጃ

የጨረታ ሰነድ የሚገኝበት ቦታ ////ጤና ጣቢያ መሳለሚያ እህል በረንዳ ከእሳት አደጋ በስተጀርባ በሚገኘው ግዥ ቢሮ ቁጥር 5 በአካል በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡

ለበለጠ መረጃ ደውለው መየት ችላሉ ስልክ ቁጥር 0112756204

 

የአዲስ ከተማ ጤና ጣቢያ

 

Save Tender