ዓባይ ባንክ አ.ማ በደሴ ከተማ ባስገነባው G+5 ህንጻ ውስጥ ከ1ኛ ወለል ጀምሮ እስከ 3ኛ ወለል (ፎቅ) ድረስ ያሉ ለአገልግሎት የተዘጋጁ ክፍሎችን ለቢሮ እና ንግድ ስራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል።
የህንፃ ኪራይ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር :- AB/PPM/05/06/2025-26
ዓባይ ባንክ አ.ማ በደሴ ከተማ ባስገነባው G+5 ህንጻ ውስጥ ከ1ኛ ወለል ጀምሮ እስከ 3ኛ ወለል (ፎቅ) ድረስ ያሉ ለአገልግሎት የተዘጋጁ ክፍሎችን ለቢሮ እና ንግድ ስራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል። በመሆኑም፡-
- ተጫራቾች የሚከራዩ ክፍሎችን ዓይነትና ስፋት ዝርዝር መግለጫ በጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ ዓባይ ባንክ ቅርንጫፍ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ከነሀሴ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ጨረታው እስከሚዘጋበት ድረስ በአካል በመቅረብ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከ2፡00 እስከ 11፡00 እና ቅዳሜ እስከ 6፡00 ዓባይ ባንክ ደሴ ከተማ መናፈሻ አካባቢ በሚገኘው ደሴ ዲትሪክት ቢሮ ወይም ባምቢስ ኖክ ፊት ለፊት በሚገኘው ዓባይ ባንክ ዋና መ/ቤት 8ኛ ፎቅ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዲፓርትመንት መግዛት ይችላሉ።
- የጨረታ መዝጊያ ቀን ነሀሴ 15 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ሲሆን የጨረታ መክፈቻ በተመሳሳይ ቀን ነሀሴ 15 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ደሴ ከተማ ዓባይ ባንክ ደሴ ዲስትሪክት ቢሮ ይከፈታል።
- የጨረታ ሰነድ የሚገባው እና የሚከፈትበት ቦታ ደሴ ከተማ በሚገኘው ዓባይ ባንክ ደሴ ዲስትሪክት ቢሮ ይሆናል፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናን በተመለከተ ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ክፍሎች ካሬ ሜትር ጠቅላላ የስድስት ወር የኪራይ ዋጋን ታሳቢ በማድረግ የሱን 2% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዛዣ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በዓባይ ባንክ አ.ማ ስም ማስያዝ አለባቸው።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ደሴ ከተማ በሚገኘው ዓባይ ባንክ ደሴ ዲስትሪክት ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታው በጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከሚዘጋበት ቀን እና ሰዓት ድረስ ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ለኪራይ የቀረቡ ክፍሎችን ከነሀሴ1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ነሀሴ 14 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በስራ ቀን እና ሰዓት ደሴ ከተማ መናፈሻ አካባቢ ህንፃው ባለበት ቦታ በመሄድ መጎብኘት ይችላሉ።
- ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0333110987/ 0115571760 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
ዓባይ ባንክ አ.ማ
ዓባይ-የታላቅነት ምንጭ!
