በምስራቅ ጐጃም ዞን የብቸና ከተማ ውሃና ፍሣሽ አገልግሎት ድርጅት የ6 ዓመት ማለትም ከሐምሌ 1/2012 - ሰኔ 30/2017 ዓ.ም ድረስ የፋይናንስና ንብረት ኦዲት ማስደረግ ይፈልጋል።
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በምስራቅ ጐጃም ዞን የብቸና ከተማ ውሃና ፍሣሽ አገልግሎት ድርጅት የ6 ዓመት ማለትም ከሐምሌ 1/2012-ሰኔ 30/2017 ዓ.ም ድረስ የፋይናንስና ንብረት ኦዲት ማስደረግ ይፈልጋል።
ስለሆነም:- ሥራው የ6 ዓመት ኦዲት ማስደረግ ሲሆን መሣተፍ የሚችሉ ደረጃ 2ና ከዚያ በላይ የተፈቀደላቸው ኦዲተሮች መሆን አለባቸው ተወዳዳሪዎች ቢያንስ ከ2 ውሃ አገልግሎቶች በላይ የሰሩና 2ትና በላይ የሆነ ጥሩ ሥራ አፈፃፀም የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር ይችላሉ፡፡
- የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ቲን ነበር ያላቸው፣
- መ/ቤቱ / ድርጅቱን ኦዲት ለማድረግ የሚያስችል የኦዲተርነት ሙያ ፍቃድ ያለው ፣
- ተጫራቾች ከላይ ከ1-3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከኦርጅናል ሠነዱ ጋር አያይዞ ቢሮ ቁጥር አስር በተዘጋጀው ሣጥን ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 2% በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንከ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም ጨረታው ተከፍቶ አሸናፊው ከተለየ ከ5 ቀን በኋላ ተሸናፊ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚመለስ ይሆናል ።
- የጨረታ አሸናፊው ማሸነፋ ከተገለፀበት ቀንጀምሮ ከ5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ በማስያዝ ውል መያዝ ይጠበቅባቸዋል ፡፡
- የጨረታ አሸናፊው ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማሸነፋ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ከ5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ተገቢውን ውል ማስከበሪያ ያልያዘና ውል ያልፈፀመ እንደሆነ መ/ቤቱ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ መውረስ ይችላል ፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው ቀን 3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኘበት ይከፈታል። ሆኖም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት መ/ቤቱ ጨረታውን ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን የባዕላት ቀን ከሆነ በተመሣሣይ በሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፈል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0586650376 እና 0924322937 ብቸና ከተማ ውሃና ፍሣሽ አገልግሎት ድርጅት
በምስራቅ ጐጃም ዞን የብቸና ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት
