የኢትዮጲያ ማዕደን ፣ ኮርፖሬሽን የተለያዩ መጠን(size) ያላቸውን በዋናው መስሪያ ቤት የሚገኙ ሱቆችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር-EMC/OT/THBD/RENT/01/2017
የኢትዮጲያ ማዕደን ፣ ኮርፖሬሽን የተለያዩ መጠን(size) ያላቸውን በዋናው መስሪያ ቤት የሚገኙ ሱቆችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡
|
ሎት |
የእቃው አይነት |
ብዛት |
ሱቁ የሚገኝበት ቦታ |
የጨረታው መዝጊያ |
የጨረታው መክፈቻ |
ጨረታው ሚከፈትበት ቦታ |
||
|
ቀን |
ሰዓት |
ቀን |
ሰዓት |
|||||
|
1 |
የተለያዩ መጠን (size) ያላቸውን ሱቆች |
24 |
አዲስ አበባ |
21/12/2017 |
4፡00 ጠዋት |
21/12/2017 |
4፡30 ጠዋት |
አ.አ ዋናው መስሪያ ቤት
|
ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው ግዴታዎች (መመሪያዎች)፡-
1. የጨረታ ሠነዱን በዚህ ማስታወቂያ በስተመጨረሻ በተገለጸው በኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት ብሎከ 2፣ በሚገኘው የኮርፖሬሽኑ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በግንባር በመገኘት የማይመለስ ብር 300.00/ ሶስት መቶ ብር/ በመከፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
2. የጨረታ ሰነድ የገዙ ተጫራቾች ለኪራይ የተዘጋጁትን ሱቆች ዘወትር በሥራ ሰዓት ከ2፡ 30 እስከ 11፡00 ሰዓት ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ጨረታውን ለመከፈት አንድ ቀን እስኪቀረው ድረስ ሱቆች በሚገኙበት ቦታዎች በአካል በመገኘት ኮርፖሬሽኑ በሚመድበው ሰራተኛ አስጎብኚነት መመልከት ይችላል፡፡
3. ተጫራቾች ለሚከራዩት ሱቆች የሰጡትን ጠቅላላ ዋጋ ብር 20,000( ሃያ ሺ ብር ) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ብቻ ከጨረታ ሠነዱ ጋር በማያያዝ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በጨረታ ሣጥኑ ውስጥ ከሰነዳቸው ጋር የማስገባት ግዴታ ይኖርባቸዋል። አሸናፊ ለሆኑትና ያስያዙት ሲፒኦ (CPO) ህጋዊ ባንከ ከሆነ በሚከፍሉት ዋጋ ውስጥ ሊታሰብላቸው ይችላል ወይም ለተሸነፉት ተመላሽ ይደረጋል፡፡
4. የጨረታ አሸናፊዎች ለሱቅ ኪራይ ቅድሚያ ስድስት ወራት የሚከፍሉ ይሆናል።
5. ከጨረታ መዝጊያ ሰዓት በኋላ የሚቀርቡ የመጫረቻ ሠነዶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡
6. ተጫራቾች የመጫረቻ ሠነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በላዩ ላይ ድርጅቶች ከሆኑ ማህተም ያረፈበት ፣ ግለሰቦች ከሆኑ ደግሞ ሶስት ፊርማ በመፈረም ማቅረብ አለባቸው፡፡
7. ተጫራቹ ሲወዳደር የሱቆቹን ስፋት እና ዋጋውን በግልጽ መሙላት ይጠበቅበታል። ግልጽ መለኪያ እና ዋጋ ያላስቀመጠ ተወዳዳሪ ከጨረታው ይሰረዛል፡፡
8. የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ ቀንን በተመለከተ ከላይ በሰንጠረዥ ዋናው መ/ ቤት በተገለጸው ቀን እና ሰዓት መሰረት ከጠዋቱ በ4፡00 ታሽጎ ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4፡30 በዋናው መ/ቤት ይከፈታል።
9. ተጫራቾች ለሚከራዩት ሱቆች ካሬ ሜትር ዋጋ በቁጥርና በፊደል ስርዝ ድልዝ የሌለበት ገልጸው በታሸገው ኤንቨሎፕ ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው። ተጫራቾች ጠቅላላ ዋጋ ማስቀመጥ የሚኖርባቸው ሲሆን ገዥ የሚሆነው የነጠላ ዋጋው ይሆናል፡፡
10. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልከ ቁጥር 0911622263 ወይም 0911091078 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
11. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
12. ሱቆችን ዘወትር በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡00 ድረስ በአካል በመቅረብ ማየት ይቻላል፡፡
13. ተከራዮች ሱቆችን ለጌጣጌጥ፣ ለማዕድን ውጤቶች፣ ለባህላዊ አላባሳት እና ቅርጻቅ ርጾች መሸጫ የሚከራዩ ይሆናል፡፡
14. ተከራዩ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ሊኖረው ይገባል።
አድራሻ፦ 22 ማዞሪያ አውራሪስ ሆቴል አጠገብ
ስልክ ቁጥር:- +251-0911622263 /0911091078
የኢትዮጵያ ማዕድን ኮርፖሬሽን
አዲስ አበባ
