Tender Detail

Tender Details

  • Company ZEMEN CONSTRUCTION CORPORATION (ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን)
  • Address ባ/ዳር ከተማ ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ቀበሌ 11 (ባህር ዳርዩኒቨርሲቲ ጥበብ ህንጻ አካባቢ የቀድሞው የአማራ ከተሞች ልማት አ.ማ ግቢ ውስጥ) እና አዲስ አበባ ለገሀር አመልድ ኢትዮጵያ ህንጻ 7ኛ ፎቅ በሚገኘው ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ቢሮ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 058-218-0538
  • Websitehttps:// zcc.org.et
  • Deadline29 Aug 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • opening date2025-08-29 00:00:00
  • Categories Electrical And Electromechanical , Mechanical Work and Materials

ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን እየገነባው ላለው ለባህር ዳር ገቢዎች ቢሮ ግንባታ ፕሮጀክታ አገልግሎት የሚውሉ የኤሌክትሮ መካኒካል (AC system) አቅርቦት እና ገጠማ ስራ ግዥ ለመፈጻም ህጋዊና ብቃት ያላቸው ፋብሪካዎችና አቅራቢዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡


 

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡- 02/2018

 

ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን እየገነባው ላለው ለባህር ዳር ገቢዎች ቢሮ ግንባታ ፕሮጀክታ አገልግሎት የሚውሉ የኤሌክትሮ መካኒካል (AC system) አቅርቦት እና ገጠማ ስራ ግዥ ለመፈጻም ህጋዊና ብቃት ያላቸው ፋብሪካዎችና አቅራቢዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን፤

  1. በዘርፉ ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያለው/ያላት፤ ጨረታ ለመሳተፍ የታክስ ክሊራንስ ያለው/ያላት፤
  2. የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን ቫትን ጨምሮ 2% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  3. የጨረታ ሰነዱን /ዳር ከተማ ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ቀበሌ 11 እና /አበባ ለገሃር አመልድ ህንፃ በሚገኘው ማስተባበሪያ /ቤት ቢሮ 7 ፎቅ ለተጠቀሱት ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ ቀናት መውሰድ ይችላሉ፡፡
  4. የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ ቀናት ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ቴክኒካል እና ፋይናንሻያል ሰነዶች ኦሪጅናልና ኮፒውን በመለየት በተለያዩ ፖስታዎች በጥንቃቄ በማሸግ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን (15 ተከታታይ ቀናትን በመቁጠር) ድረስ ብቻ ባህር ዳር ዋናው ቢሮ 1 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 104 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ከላይ በተጠቀሱት ቀናት 800 ሰዓት ሳጥኑ ታሽጎ 830 ሰዓት ይከፈታል። የተጠቀሱት የመክፈቻ እና የመዝጊያ ቀናቶች የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን እስከ ቀኑ 800 ሰዓት ድረስ ማስገባት የሚችሉ ሲሆን በእለቱ 800 ሰዓት ሳጥኑ ታሽጎ 830 ሰዓት ይከፈታል፡፡
    1. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ውስጥ ከዚህ በፊት የኤሌክትሮ መካኒካል (AC system) በብቃት እና በጥራት ለመስራታቸው የሚያረጋግጥ የመልካም ስራ አፈፃፀም ማያያዝ ግዴታ መሆኑን መታወቅ አለበት፡፡
  5. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡

ለማንኛውም ተጨማሪ ማብራሪያ ስልክ ቁጥር፡-

ባህር ዳር:- 058-218-0538/ 09-13-27-60-57/ 09-18-71-66-16

አዲስ አበባ፡- 011-126-5338/ 09-30-35-24-10/ 09-67-99-42-10

 

የዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን

 

 

Save Tender