በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት በእያንዳንዱ የጣውላ ዓይነት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
የጣውላ ምርት ግልጽ ጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር OFWE/XA 02/2018
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት በእያንዳንዱ የጣውላ ዓይነት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ
- በአርሲ ቅ/ጽ/ቤት በተለያዩ የእንጨት መሰንጠቂያ ላይ የተዘጋጀ ጣውላ ፤
- በጅማ ቅ/ጽቤት በተለያዩ የእንጨት መሰንጠቂያ ላይ የተዘጋጀ ጣውላ ፤
- በባሌ ቅ/ጽ/ቤት በተለያዩ የእንጨት መሰንጠቂያ ላይ የተዘጋጀ ጣውላ፤
- በቦረና ጉጂ ቅ/ጽ/ቤት በተለያዩ የእንጨት መሰንጠቂያዎች ላይ የተዘጋጀ ጣውላ፤
- በፊንፊኔ ቅ/ጽ/ቤት በተለያዩ የእንጨት መሰንጠቂያ ላይ ተከፋፍሎ የተዘጋጀ ጣውላ፤
- በሐረርጌ ቅ/ጽ/ቤት በተለያዩ የእንጨት መሰንጠቂያ ላይ ተከፋፍሎ የተዘጋጀ ጣውላ፤
- በኢሉአባቦራ ቅ/ጽ/ቤት በተለያዩ የእንጨት መሰንጠቂያ ላይ የተዘጋጀ ጣውላ፤
- በወለጋ ቅ/ጽ/ቤት የእንጨት በተለያዩ የእንጨት መሰንጠቂያ ላይ የተዘጋጀ ጣውላ፤
በመሆኑም
- የጣውላ የቤትና የቢሮ እቃዎችና ተዛማጅ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው ድርጅቶች እና ግለሰቦች እንዲሁም Tin number ያላቸውና እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ ስለ ጨረታው ዝርዝር ሁኔታ የሚገለጽ የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዳቸው 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ቀበና ሼል /አይል ሊቢያ/ አጠገብ በሚገኘው የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ዋና መቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 እና ጨረታው በሚውበት በጂማ ቅ/ጽ/ቤት (ጂማ) በኢሉአባቦራ ቅጽ ቤት (መቱ) በአርሲ ቅጽቤት (አርሲ ነጌለ) ፊንፊኔ ቅ/ጽ/ቤት (ፊንፊኔ) በሐረርጌ ቅጽ ቤት (ጭሮ) በቦረና ጉጂ ቅ/ጽ/ቤት (አዶላ) በባሌ ቅ/ጽ/ቤት (ጎባ) በወለጋ ቅጽ ቤት (ግምቢ) በመግዛት በጨረታው መሣተፍ ይችላሉ።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆያል።
- ጨረታው የሚዘጋበት እና የሚከፈትበት ቀንና ሰዓት በጨረታው ሰነድ ውስጥ ይገለጻል።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid bond) የሚሆን ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ 5% በማስላት በድርጅቱ ዋና መ/ቤት የምትጫረቱ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ከሚገኙ ባንኮች በቅ/ጽ/ቤት የምትጫረቱ መ/ቤቱ ከሚገኝበት ከተማ በባንክ በተረጋገጠ ደረሰኝ (cpo) ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
- ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 124 0249 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት
