የሀድያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለዞኑ ባህል ቱሪዝም መምሪያ ለሀድያ ብሔር ዘመን መለወጫ ያሆዴ ክብረ በዓል አከባበር የሚሆን ባህላዊ አልባሳት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የሀድያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለዞኑ ባህል ቱሪዝም መምሪያ ለሀድያ ብሔር ዘመን መለወጫ ያሆዴ ክብረ በዓል አከባበር የሚሆን ባህላዊ አልባሳት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡
በዚሁ መሠረት ተጫራቾች፡-
፲ኛ በመስከ የታደሰ ንግድ ፈቃድ
2ኛ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር
3ኛ, የዕቃ አቅራቢነት ሰርተፍኬት ያላቸው ድርጅቶች፤
በሀድያ ዞን ፋ/መምሪያ ቢሮ ቁጥር 17 በአካል በመቅረብ የተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ብር 200/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል እንድትገዙና ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 30,000/ሠላሳ ሺህ ብር በባንክ የተረጋገጠ (CPO) ማስያዝ የሚጠበቅባቸው ሲሆን የጨረታ መወዳደሪያ መምሪያው ባዘጋጀው ፎርማት ላይ ብቻ በመሙላት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የመወዳደሪያ ፖስታዎችን ኦርጅናልና ኮፒ በማሸግ ቢሮ ቁጥር 17 ላይ በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እንድታስገቡና ጨረታውም በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ የጨረታ ሳጥን ታሽጎ በ4፡30 ላይ የሚከፈት ሲሆን ቀኑ የእረፍት ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ ቀን በተመሳሳይ ቦታና ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር
0461784281/0465552337
ደውሎ መጠየቅ የሚቻል መሆኑን እንገልጻለን።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የሀድያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ሆሳዕና
