የኦሮሚያ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ የተለያዩ የእህል (የበቆሎ እና ዳጉሳ) አጨዳና ማጓጓዝ አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የወጣ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር OSE/NCB/002/2018
የኦሮሚያ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ የተለያዩ የእህል (የበቆሎ እና ዳጉሳ) አጨዳና ማጓጓዝ አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም አስፈላጊውን መስፈርት የምታሟሉ በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን ተጫራቾች፡
-
የንግድ ምዝገባ ሰርቲፊኬት
-
የዘመኑን የታደሰ ንግድ ፈቃድ
-
የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርቲፊኬት
-
የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin No)
-
የአቅራቢነት ማስረጃ (Suppliers List)
-
የሚፈለግባቸውን የመንግሥት ግብር ስለመወጣታቸው የሚገልጽ ማስረጃ፣ ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዳቸውጋር በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው፡፡
ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለı5 ተከታታይ ቀናት ሰነዱን በመግዛት በ16ኛ የሥራ ቀን ጨረታው የሚዘጋና የሚከፈት ይሆናል፡፡የጨረታ ሰነድ መግዣ ዋጋ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) መሆኑን እየገለጽን፤ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያቸውን በፖስታ በማሸግ በተጠቀሱት ቀናት ከጠዋቱ 2፡30-8፡00 ሰዓት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በማስገባት በጨረታው እንድትሳተፉ እንጋብዛለን፡፡ የጨረታ ሳጥኑ ከላይ በተጠቀሱት ቀናት 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢንተርፕራይዙ ዋና መ/ቤት ጎተራ አጎና ሠራዊት ሲኒማ አጠገብ ባለኬር ሕንፃ /Baleker Tower/ 4ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የኦሮሚያ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ ቢሮ ቁጥር 402 ይከፈታል፡፡፡ ኢንተርፕራይዙ የተሻለ አማራጭ ካገ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የኢንተርፕራይዙ የሥራ ሰዓት ከሰኞ-ዐርብ ጠዋት ከ2፡30-6፡30 ከሰዓት በኃላ ከ7፡30-11፡30 ነው።
ለበለጠ ማብራሪያ፡-ስ.ቁ 011-416 03 09/011-466-25-27 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የኦሮሚያ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ
