ድርጅታችን የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት (ኢኢግልድ) የfortigate firewall software license እድሳት ግዥ ከconfiguration እና ሥልጠና የአገልግሎት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
ብሔራዊ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር ኢኢግልድ 003/2018
ድርጅታችን የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት (ኢኢግልድ) የfortigate firewall software license እድሳት ግዥ ከconfiguration እና ሥልጠና የአገልግሎት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስና የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ በመንግስት ግዢና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ዝርዝር የተመዘገቡበት የምስክር ወረቀትና ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን በጨረታ እንዲሳተፍ የተፃፈለትን የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል መሆን ይኖርበታል፡፡
ለዚህ የተዘጋጀውን ዝርዝር የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሦስት መቶ) በመክፈል ከድርጅቱ ግዢ ቡድን በመቅረብ መውሰድ ይችላል፡፡
ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው የfortigate firewall software license እድሳት ግዥ ከconfiguration እና ሥልጠና የአገልግሎት ግዥ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ኦርጅናል እና ኮፒ ሰነዶች በተለያዩ ፖስታዎች በማድረግ እንዲያቀርቡ እያሳሰብን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ በማግስቱ በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢኢግልድ ዋና መ/ቤት ስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 11ኛው ቀን በዓል ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
ተጫራቾች በጨረታ ለመወዳደር የጨረታ ማስከበሪያ ብር 30,000 (ሠላሳ ሺህ ብር ብቻ) የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት (Ethiopian Industrial Inputs Development Enterprise) ስም በሲ.ፒ.ኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከጨረታው ቴክኒካል ሰነድ ጋር በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው፡፡
ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ ፡- በኢኢግልድ ዋና መ/ቤት ፒያሳ ከሊፋ ሕንፃ አካባቢ በስተሰሜን አቅጣጫ የባቡር ሃዲዱን ተሻግሮ (የቀድሞ ጅንአድ) አራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 2።
ተጨማሪ ማብራሪያ ቢያስፈልግ፡- በስልክ ቁጥር 0111-57-24-97 በመደወል ወይም በአካል በመቅረብ ይችላሉ፡፡
የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት
