Tender Detail

Tender Details


የመቂ ከተማ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት በ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ የጽፈት መሳሪያ፣ የፅዳት ዕቃ፤ የቧንቧ መገጣጠሚያ (Fitting)፣ የውሃ ቧንቧ መስሪያ ዕቃዎች (Tools)፣ የኤሌክትሪክ ዕቃ፣ የባጃጅ ስፔር ፓርት፣ የላብራቶሪ ዕቃዎች (Laboratory)፣ ፓንፕ /Pump/፣ የደንብ ልብስ፣ ማውንቴን ሳይከል፣ ሱዚኪ ኬሪ ባጃጅ ባለ 4 እግር፣ የጭነት መኪና፣ ላፕቶፕ፣ ኮምፒውተር፣ ፕሪንተር፣ ከለር ፕሪንተር፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች እና የቢሮ ወንበሮች /Furniture/ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡


የጨረታ ማስታወቂያ

የመቂ ከተማ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት በ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ የጽፈት መሳሪያ፣ የፅዳት ዕቃ፤ የቧንቧ መገጣጠሚያ (Fitting)፣ የውሃ ቧንቧ መስሪያ ዕቃዎች (Tools)፣ የኤሌክትሪክ ዕቃ፣ የባጃጅ ስፔር ፓርት፣ የላብራቶሪ ዕቃዎች (Laboratory)፣ ፓንፕ /Pump/፣ የደንብ ልብስ፣ ማውንቴን ሳይከል፣ ሱዚኪ ኬሪ ባጃጅ ባለ 4 እግር፣ የጭነት መኪና፣ ላፕቶፕ፣ ኮምፒውተር፣ ፕሪንተር፣ ከለር ፕሪንተር፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች እና የቢሮ ወንበሮች /Furniture/ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሠረት ከዚህ በታች የተገለፀውን መስፈርት የሚያሟሉ ድርጅቶች እንዲካፈሉ ተጋብዘዋል፡፡

1. ተጫራቾች በጨረታው ለመካፈል በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና ግብር የከፈሉ፤

2. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታከስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ እና የንግድ መለያ ቁጥር (TIN Number) ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

3. ተጫራቾች የአቅራቢነት የምስከር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

4. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኃላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለፀውን ማንኛውንም ሁኔታዎች መለወጥ ወይም ማሻሻል ወይም ጨረታውን ትቻለሁ ማለት አይችልም፡፡

5. የሚገዙ ዕቃዎች በተሰጠው እስፔስፊኬሽን መሰረት አሟልቶ ላልቀረበና ማንኛውንም ስህተት ቢፈፅም ኃላፊነቱ የተጫራቹ /የአቅራቢው/ ድርጅት ይሆናል፡፡

6. ለጨረታው የሚቀርበው ሰነድ ስርዝ ድልዝ የሌለው ሆኖ የሚቀርበው ዋጋ በግልፅ መፃፍ ይኖርበታል፡፡ እንዲሁም የመቂ ከተማ መጠጥ ውሃ አገልግሎት ድርጅት ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ ብቻ ዋጋ መሞላት አለበት፡፡

7. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበሪያ በየሎቱ ብር 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር) CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

8. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ሰነድ ላይ ያቀረበው ዋጋ ለሶስት (3) ወር ፀንቶ የሚቆይ ሲሆን የዋጋ ለውጥ የሚካሄደው ከሶስት ወር በኃላ በገበያ ጥናት አሸናፊው ድርጅት በሚያቀርበው ዋጋ ተንተርሶ በሚሰጥ ዋጋ ይሆናል፡፡

9. አሸናፊው ድርጅት ውል በገባ በo ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዕቃውን በድርጅቱ መስሪያ ቤት ገቢ ማድረግ ይኖርበታል፡፡

10. ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው ዕቃዎች ሙሉ በሙሉ ኦሪጅናል መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

11. ተጫራቾች የጨረታ ሰንዱን የማይመለስ ብር 700 (ሰባት መቶ ብር) በመከፈል መግዛት ይችላሉ፡፡

12. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናውንና ኮፒውን ቴክኒከና ፋይናንስ በተናጠል በታሸገ ኤንቨሎፕ አሽገው ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን የድርጅቱን ማህተም ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡

13. የጨረታ ሰነዱ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስራ አምስት (15) ተከታታይ የስራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው (አስራ ስደስተኛው) የስራ ቀን በ6፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት በ8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

14. አሸናፊው ድርጅት ባሸነፈባቸው ዕቃዎች ከጠቅላላ ዋጋ 10/100 ለድርጅቱ ውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

15. ማንኛውም ተጫራች የሚወዳደሩባቸውን ዕቃዎች በአካል ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

16. ከዚህ በላይ በተገለጸው መሰረት ተጫራቾች የጨረታ ግዴታ ባይወጡ ወይም ውሉን በአግባቡ ሳይፈጽሙ ቢቀሩ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ በግዥ መመሪያ ቁጥር 02/2001 እና FA 1/2009 እንዲሁም አዋጅ ቁጥር 157/2002 መሠረት ጽ/ቤቱ ህጋዊ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን ማወቅ ይኖርባቸዋል፡፡

17. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ማሳሰቢያ፡-

የሚፈለገው የዕቃ ብዛት የምናሳወቀው የማሸነፊያ (የጨረታ) ዋጋ ከተለያ በኃላ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

  • ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ዋጋ ከቫት ጋር መሆኑን እና አለመሆኑን የጨረታ ሰነዱ ላይ በግልጽ መፃፍ ይኖርበታል፡፡

ስበስጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 09-12-99-94-99 እና 09-12-30-94-52 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

አድራሻ፡- ምሥራቅ ሸዋ ዞን መቂ ከተማ የመቂ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት

የመቂ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት

Save Tender