በአራዳ ከፍለ ከተማ አስተዳደር የሚገኘው የጃንሜዳ ጤና ጣቢያ 001/2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ዙር ግልፅ ጨረታ በጤና ጣቢያችን የሚገኙ እቃዎችን እና አገልግሎቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በአራዳ ከፍለ ከተማ አስተዳደር የሚገኘው የጃንሜዳ ጤና ጣቢያ 001/2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ዙር ግልፅ ጨረታ በጤና ጣቢያችን የሚገኙ እቃዎችን እና አገልግሎቶችን ማለትም፡-
1. ሎት 1 - የደንብ ልብስ፤
2. ሎት 2 - ህትመት፤
3. ሎት 3 - አላቂ የቢሮ እቃዎች፤
4. ሎት 4 - አላቂ የህክምና እቃዎች፤
5. ሎት 5 - የፅዳት እቃዎች፤
6. ሎት 6 - ቋሚ የህከምና እቃዎች፤
7. ሎት 7 - ቋሚ የቢሮ እቃዎች፤
8. ሎት 8 - የጥገና እቃዎች፤
9. ሎት 9 - የጀነሬተር ጥገና፤
10. ሎት 10 - የላውንደሪ ማሽን ጥገና፤
11. ሎት 11 - የፈሳሽ ቆሻሻ ማንሳት፤
12. ሎት 12 - የህክምና እቃዎች ጥገና፤
13. የአገልግሎት ጊዜያቸው ያለፋባቸው መድሐኒቶችን ማስወገድ ሲሆኑ ስራዎቹን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሰረት ለመጫረት የምትፈልጉ-
1. በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው፤
2. በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ፤
3. የታደሰ ህጋዊ ፈቃድ ወይም የዘመኑን ግብር ከፋይ የሆኑ፤
4. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፤
5. የጨረታ ሰነድ ዋጋ ብር 300.00 ብር /ሶስት መቶ ብር/ ብቻ ነው፡፡
6. የጨረታ ማስከበሪያ ዋጋ፡-
ሎት1..........20,000.00
ሎት2..........10,000.00
ሎት3..........20,000.00
ሎት4..........30,000.00
ሎት5………....20,000.00
ሎት6.......... 70,000.00
ሎት7………….50,000.00
ሎት8……......20,000.00
ሎት9............50,000.00
ሎት 10………..40,000.00
ሎት11…………..20,000.00
ሎት12…….......20,000.00
ሎት13........50,000
7. ተጫራቾች የሚያስገቡት ዋጋ VAT 15% ያካተተ መሆን ይኖርበታል፡፡
8. ተጫራቾች የጨረታ መወዳደሪያ ማቅረቢያ ጊዜ የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ቀናት በጃንሜዳ ጤና ጣቢያ ውስጥ በፋይናንስ ከፍል ቢሮ ቁጥር 227 በመግዛት በታሸገ ፓስታ ማስገባት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው በ11ኛው የስራ ቀን በ4፡00 ሰዓት ሳጥኑ ታሽጎ በ4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሰነዱ ይከፈታል፡፡
9. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
10. ፋይናንሻል ኦሪጅናል እና ፋይናንሻል ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
11. የሚጠገኑትን እቃዎች ንብረቶቹ ባሉበት ቦታ በማየት ሲሆን የጥገና ዋጋው ለሰርቪሱ የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን ያካተተ መሆን አለበት፡፡
12. ለበለጠ መረጃ ዝርዝር መረጃ ሰነዱ ላይ መመልከት ይችላሉ፡፡
አድራሻ፡- ከ6 ኪሎ ወደ ጃንሜዳ የሚወስደው መንገድ ከቴሌ ፊት ለፊት አራዳ ከፍለ ከተማ ጃንሜዳ ጤና ጣቢያ ቢሮ ቁጥር 227
የጃንሜዳ ጤና ጣቢያ
