መገዘዝ ንግድና የማማከር ስራዎች ኢንተርፕራይዝ ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን አቅርቦት ከአምራች ወይም አቅራቢ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በድጋሚ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
መገዘዝ ንግድና የማማከር ስራዎች ኢንተርፕራይዝ ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን አቅርቦት ከአምራች ወይም አቅራቢ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- በመሆኑም ከዚህ በታች በሎት ለተዘረዘሩት ጨረታዎች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከታወቀ ባንክ የሚሰጥ የክፍያ ማዘዣ ቼክ /ሲፒኦ/ ለእያንዳንዱ ሎት በተቀመጠው የገንዘብ መጠን በመገዘዝ ንግድና የማማከር ስራዎች ኢንተርፕራይዝ ስም በማሰራት ከዋናው የዋጋ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
|
ተ.ቁ |
ሎት |
የጨረታ ማስከበሪያ የብር መጠን |
|
1 |
ሎት አንድ፡- ድፍን ምስር |
100,000.00 |
|
2 |
ሎት ሁለት፡- ድፍን አተር |
100,000.00 |
|
3 |
ሎት ሶስት፡- ድፍን ባቄላ |
100,000.00 |
|
4 |
ሎት አራት፡- የውጭ ሩዝ |
100,000.00 |
|
5 |
ሎት አምስት፡- በቆሎ |
100,000.00 |
|
6 |
ሎት ስድስት፡- የዳቦ ዱቄት |
100,000.00 |
|
7 |
ሎት ሰባት፡- ኬሻ ማዳበሪያ ከነህትመቱ |
100,000.00 |
|
8 |
ሎት ስምንት፡- የእንሰሳት መኖ ማቀነባበሪያ ግብዓት |
100,000.00 |
|
9 |
ሎት ዘጠኝ፡ - የኦዲት አገልግሎት |
20,000.00 |
- ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ፣ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢው ባለስልጣን የተሠጠ የምስክር ወረቀት እና አቅራቢዎች አምራች ወይም ኤጀንት ከሆኑ በጨረታ ሰነዱ የተጠቀሱ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው። እንዲሁም ለሎት ስድስት ከፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የተፈቀደና የታደሰ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሠዓት እስከ ቀኑ አስር ሠዓት ድረስ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ከመገዘዝ ንግድና የማማከር ስራዎች ኢንተርፕራይዝ ግዥ ቡድን ቢሮ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሣባቸውን የያዘ የዋጋ ሰነድ ዋናና ቅጅ ለየብቻው በታሸገ ኢንቨሎኘ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ቀናት እስከ 15ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ በኢንተርፕራይዙ ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲሁም ጨረታውን መታዘብ የሚፈልግ ማንኛውም አካል በተገኙበት ማስታወቂያው በወጣ በ15ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 በኢንተርፕራይዙ ግዥ ቡድን ቢሮ በግልፅ ይከፈታል። የመክፈቻው ቀን በሳምንቱ የዕረፍት ቀናት ወይም በዓል ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለፀው ሰዓትና ቦታ በግልፅ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተመስርተው የመወዳደሪያ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም።
- የጨረታው ውጤት ለአሸናፊና ለተሸናፊ ተጫራቾች በእኩል ጊዜ በውስጥ ማስታወቂያ እና በደብዳቤ ይገለፃል፡፡
- ኢንተርፕራይዙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥራችን /+251912211682/ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በደ/ብርሃን ዩኒቨርሲቲ መገዘዝ ንግድና የማማከር ስራዎች ኢንተርፕራይዝ
