Tender Detail

Tender Details

  • Company SPA SERVICE ENTERPRISE (የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት)
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 5 51 91 00
  • Websitehttps://www.filwuha.gov.et/
  • Deadline19 Sep 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • opening date2025-09-19 00:00:00
  • Categories Land, House, Building And Warehouse Rent

የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ከዚህ በታች የተገለፁትን የተለያዩ የዕቃ ግዥ /አገልግሎት/ ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችንአወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ

የጨረታ ማስታወቂያ

የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ከዚህ በታች የተገለፁትን የተለያዩ የዕቃ ግዥ /አገልግሎት/ ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችንአወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

በዚህም፡-

ለመጀመሪያ ጊዜ ጨረታ የሚወጡ የዕቃ/ የአገልግሎት ግዥ

ሎት: ለቨርቹዋል ባንኪንግ የሚሆን ቦታ ኪራይ

ተጫራቾች የሚከተሉትን መመሪያዎች ማሟላትና ተግባራዊ ማድረግ አለባቸው፤

1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበት ሕጋዊና የታደሰ የ2017 ዓ.ም ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብርስለመከፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

2. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ TIN እና VAT ሰርተፊኬት ያላቸው፤ የገቢዎች ከሊራንስና ጨረታ ለመሳተፍ ከሐገር ውስጥ ገቢ የተሰጣቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ ለቨርቹዋል ባንኪንግ አገልግሎት ለመስጠት ከሚመለከተው አካል የተሰጠ ፈቃድና የተመዘገቡበት የቅርብ ጊዜ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

3. ማንኛውም ተጫራች የግዥ ጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ CPO ብቻ ማስያዝ አለባቸው፡፡

4. ለጨረታ ሰነድ መግዣ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በድርጅታችን አዲሱ ፍልውሃ ሆቴል እንግዳ መቀበያ በመክፈል ከድርጅቱ ግዥ አቅርቦት ቡድን መሪ ቢሮ ቀርበው የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡

5. ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ከሻት በፊትና ከነቫቱ ተብሎ በኢትዮጵያ ብር መገለጽ አለበት። ተጫራቾች በጨረታ ሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን፣ መሉ አድራሻቸውን፣ ፊርማቸውንና ማህተም አሟልተጡ ማቅረብ አለባቸው...

6. ጨረታው ከተከፈት በኋላ በጨረታ ሰነድ ላይ የተሰጠ ዋጋን መለወጥ አይቻልም፤ ዕቃው የሚቀርብበት ጊዜ፣ ቦታና ዋጋው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ መገለጽ አለበት፡፡ ስለ ዕቃው ዋስትናና የዋስትና ጊዜ በግልጽ መገለጽ አለበት፡፡

7. ጨረታውን በሚመለከት ለማሸነፍ እንዲረዳው ለማንኛውም ኃላፊና ሠራተኛ መደለያ የሰጠ ተጫራች ከጨረታው የሚሰረዝ ሲሆን አሸንፎም ውል ቢዋዋል ውሉ ይሰረዛል፡፡

8. ድርጅታችን የዋጋ ለውጥ ሳይኖር በመጠን ወይም በዋጋ እስከ 25% በመጨመር ወይም እስከ 20% በመቀነስ መግዛት እንደሚችል በቅድሚያ መታወቅ ይኖርበታል።

9. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ከቫት በፊት ወይም ከቫት ጋር በግልጽ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም 09 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው በዕለቱ ጠዋት 4:30 ይከፈታል።

10. ተጫራቾች በሚጫረቱበት የግዥ አይነት መሠረት የተሟላ የቴከኒካል ሰነድ እና ፋይናሻል በተዘጋጀ የጨረታ ሰነድ /Bid document /መሠረት የጨረታ ሰነዳቸውን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታው ቴክኒካል ፕሮፖዛል ሰነድ ለብቻው የጨረታ ማስከበሪያ CPO/ ለብቻ እና ፋይናሻል ሰነድ ለብቻው በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡

11. የጨረታ ሂደቱ የቴከኒከ ግምገማ ድርጅቱ በሚያወጣው መስፈርት መሠረት ቴከኒካል ሰነድ ግምገማ ውጤት 40% እና የፋይናንሻል (ዋጋ) ግምገማ ውጤት (60%) ድምር ውጤት አሸናፊ የሚለይ መሆኑን ማወቅ አለባቸው፡፡ ነገር ግን ቴከኒካል ግምገማ ያላለፈ ተጫራች /ድርጅት ፋይናንሻል እንደማይከፈት እንዲታወቅ የመገምገሚያ መስፈርቶቹ በሚሸጠው የጨረታ ሰነድ ማየት ይቻላል፡፡

ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር on5530767/0115157337

ፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት

Save Tender