ቶታል ኢነርጂስ ማርኬቲንግ ኢትዮጵያ አ.ማ. የቀላል ተሽከርካሪ ምርመራ አገልግሎት በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የቀላል ተሽከርካሪ ምርመራ አገልግሎት ለመግዛት የወጣ ጨረታ
ጨረታ ቁጥር -T-408/25/GS/PUR
ቶታል ኢነርጂስ ማርኬቲንግ ኢትዮጵያ አ.ማ. የቀላል ተሽከርካሪ ምርመራ አገልግሎት በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በጨረታው መካፈል የሚፈልግ ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ቅድመ ሁኔታዎች በማሟላት መጫረት ይችላል።
- ተጫራቾች ከሚመለከትው ባለስልጣን የሙይ ማረጋገጫ ፍቃድ፤ የታደሰ የንግድ ፍቃድ፤ የቲን ምስክር ወረቀት እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ምዝገባ ሊኖራቸው ይገባል።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ክቫት በፊት ከተጠቀሰው ዋጋ ላይ 2% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ወይም C.P.O. ከጨረታው ስነድ ጋር ማስገባት አለባቸው።
- በጨረታ ሰነዱና በC.P.O ላይ የሚጠቀሰው የተጫራች ስም አንድ ዓይነት መሆን አለበት::
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ (ቴክኒካል እና ፋይናሻል) በተለያየ ፖስታ አሽገው፤ ፖስታው ላይ የተጫራቹን ስም ፤ ስልክ ቁጥርና የሚወዳደሩበትን የጨረታ አይነት በፖስታው ላይ በመፃፍ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይጠበቅባቸዋል::
- ጨረታው ነሐሴ 25 ቀን 2017 ተከፍቶ መስከረም 5 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 10:00 ሰዓት ላይ ይዘጋል።
- ተጫራቾች ዝርዝር የያዘውን የጨረታ ሰነድ ሙለጌ ህንፃ ሰባተኛ ፎቅ በሚገኘው ቶታልኢነርጂስ ማርኬቲንግ ኢትዮጵያ አ.ማ. ዋናው መ/ቤት በአካል በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።
- ቶታልኢነርጂስ ማርኬቲንግ ኢትዮጵያ አ.ማ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ቶታል ኢነርጂስ ማርኬቲንግ ኢትዮጵያ አ.ማ.
ዋናው መስሪያ ቤት የግዥ ክፍል
ሳሪስ መንገድ ቡና ቦርድ ፤ ሙለጌ ህንፃ 7ኛ ፎቅ
ስልክ፣ 0114651125
