Tender Detail

Tender Details


የይ ዓለም ሆስፒታል ህከምና ኮሌጅ ተኝተውና ተመላልሰው ለሚታከሙ ህሙማን የሚውሉ መድኃኒቶች፣ የህክምና መገልገያዎችንና የላቦራቶሪ ሪኤጀንቶች፣ አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ አላቂ የዕዳት ዕቃዎችን፣ ለሠራተኞች ደንብ ልብስ፣ ለተኝቶ ታካሚዎችና ለህከምና ተማሪዎች ለምግብ አገልግሎት የሚሆኑ ጥራጥሬዎች ፣አትከልት፣ ዳቦ፣ እንጀራ ፣ የህንፃ ጥገና ቁሳቁሶች፣ ቢሮ መገልገያ ዕቃዎች (ፈርኒቸር/ቮ የመኪና መለዋወ


የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/2019

 

የይ ዓለም ሆስፒታል ህከምና ኮሌጅ ተኝተውና ተመላልሰው ለሚታከሙ ህሙማን የሚውሉ መድኃኒቶች፣ የህክምና መገልገያዎችንና የላቦራቶሪ ሪኤጀንቶች፣ አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ አላቂ የዕዳት ዕቃዎችን፣ ለሠራተኞች ደንብ ልብስ፣ ለተኝቶ ታካሚዎችና ለህከምና ተማሪዎች ለምግብ አገልግሎት የሚሆኑ ጥራጥሬዎች ፣አትከልት፣ ዳቦ፣ እንጀራ ፣ የህንፃ ጥገና ቁሳቁሶች፣ ቢሮ መገልገያ ዕቃዎች (ፈርኒቸር/ቮ የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች፣ የተለያዩ ህትመቶች፣ የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች እና የመኪናዎች ጥግና ስራ በግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለማስጠገን ይፈልጋል፡፡

1.     ህጋዊና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ፣የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና በተጨማሪ እሴት ታከስ የተመዘገቡ፡፡

2.    የጨረታ ማስከበሪያ ብር 30,000.00 /ሰላሳ ሺህ ብር/ CPO ማስያዝ የሚችሉ፡፡

3.    በጨረታ ላይ ለመወዳደር የሚያስችል ማስረጃ ከገቢዎች ቢሮ የተሰጣቸውንና የታደሰ ከሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

4.    ተጫራቾች ህጋዊ ንግድ ፈቃዳቸውን ተ.እ.ታ, የተመዘገቡበትን ሰርትፍኬት በማቅረብ የጨረታ ዶክሜንቱን ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ስራ ቀናት ውስጥ ይዓለም ሆስፒታል ህከምና ኮሌጅ ግዥ ን/አስ/ዳይሬከቶሬት ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 በመቅረብ የማይመለስ ብር 400/አራት መቶ/ በመክፈል የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡

5.    የጨረታ ሰነድ አንድ ቴክኒካል ኦርጂናል እና ሁለት ቴክኒካል ኮፒ እና እንድ ፋይናሻል ኦርጂናል ሁለት ፋይናሻል ኮፒ ሰነድ እያንዳንዱን ፖስታዎች የድርጅቱን ማህተም ተደርጎና በሰም በማሸግ በአንድ ፓስታ በማድረግ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው::

6.    የጨረታ ሰነድ በተጫራች መመሪያ መሠረት ተሞልቶ እና ቁልቁል ተደምሮ ህጋዊ የሆነ የድርጅቱን ማህተም በማሳረፍ በ16ኛ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ 6፡00 ሰዓት ድረስ ይ ዓለም ሆስፒታል ህከምና ኮሌጅ ግዥ ን/አስ/ዳይሬክቶሬት ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

7.    ጨረታው በ16ኛው ቀን ከቀኑ 6፡00 /ስድስት ሰዓት/ ላይ ተዘግቶ ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ከቀኑ 8፡00 /ስምንት ሰዓት/ ላይ በግልፅ ይከፈታል፡፡

8.    የወቅቱ የገበያ ዋጋ ያላገናዘበ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም ከቀረበው የዋጋ ትንታኔ መያዝ አለበት፡፡

9.    መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ማሳሰቢያ፦

ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡ ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 0909495415 እና 0911708366 ይደውሉ

 

በሲ/ብ/ክ/መ/ጤና ቢሮ የይ/ዓስም ሆስፒታል ህክምና ኮሌጅ

 

 

✨ messages.ai_summary
- Yirgalem Hospital Medical College (under Sidama Regional Health Bureau) invites open bids for medicines, medical supplies, laboratory reagents, consumable office supplies, staff uniforms, food items (grains, vegetables, bread, injera), building maintenance materials, furniture, vehicle spare parts, and vehicle repair works. Tender notice no. 01/2019. - Bid document price: 400 ETB (non-refundable); bid bond: 30,000 ETB via CPO. - Submission deadline: on the 16th day at 6:00 AM; bids open at 8:00 on the same specified date and place. - Eligibility includes a valid renewed business license, paid current tax, VAT registration, and a renewed clearance certificate from the revenue office.
Save Tender