Tender Detail

Tender Details

  • Company የበቾ ወሊሶ የገበሬዎች ሕብረት ስራ ዩኒየን ኃላፊነቱ የተወሰነ ማህበር
  • Address በጅማ መንገድ ከአዲስ አበባ 80ኪ.ሜ ቱሉ ቦሎ ከተማ ፡ ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን : ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0113420140
  • Website
  • Deadline22 Sep 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • opening date2025-09-22 00:00:00
  • Categories Computer Laptop And Accessories , Machinery , Vehicle

በቾ ወሊሶ የገበሬዎች ኅብረት ሥራ ዩኒየን ıኛ. የኤፍ ኤስ አር (FSR) ቅጥቅጥ የህዝብ ማመላለሻ መኪና፣ 2ኛ. የተለያየ ዓይነት ያገለገሉ እና አዲስ የፋብሪካ ማሽኖች እና የተለያዩ አይነት ያገለገሉ ኮምፒውተሮች በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡


                                                                                      የጨረታ ማስታወቂያ

 በቾ ወሊሶ የገበሬዎች ኅብረት ሥራ ዩኒየን ıኛ. የኤፍ ኤስ አር (FSR) ቅጥቅጥ የህዝብ ማመላለሻ መኪና፣ 2ኛ. የተለያየ ዓይነት ያገለገሉ እና አዲስ የፋብሪካ ማሽኖች እና የተለያዩ አይነት ያገለገሉ ኮምፒውተሮች በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም መግዛት የሚፈልግ ግለሰብ ወይም ድርጅት ከዚህ ቀጥሎ ያሉትን መስፈርቶች በማሟላት ተወዳድሮ መግዛት ይችላል፡፡ 

  1. ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው እና የዓመቱን ግብር የከፈሉ እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ 

  2. ለጨረታ ሰነድ ግዢ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በዩኒየኑ የባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000087184327 ኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ወይም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000036818348 በመክፈል ሰነዱን ከዩኒየኑ መውሰድ አለባቸው፡፡ 

  3. ለጨረታ ማስረከቢያ ቢድ ቦንድ ማስያዣ ያቀረቡትን ዋጋ 5% በሲፒኦ ወይም በባንክ ዋስትና ሰነድ ማስያዝ አለባቸው። 

  4.  ተጫራች የጨረታ ሰነዶቹን በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ 12/01/2018 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት ድረስ _ ዘወትር በሥራ ሰዓት ዩኒየኑ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡ 

  5. የጨረታ መክፈቻ ቀን 12/01/2018 ዓ.ም ከቀኑ 8:30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ 

  6.  ተጫራቾች አንዱ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው፡፡ 

  7. ዩኒየኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ 

  8. አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈውን ንብረት ሙሉ በሙሉ እስከ 10 ቀን ጊዜ ውስጥ ማንሳት ይኖርበታል፡፡ 

አድራሻ፡- በጅማ መንገድ ከአዲስ አበባ 80 ኪ.ሜ ቱሉ ቦሎ ከተማ ላይ እንገኛለን፡፡ በተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡- 0911080003/0912122971 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

                                                                   በቾ ወሊሶ የገበሬዎች ኅብረት ሥራ ዩኒየን

Save Tender