Tender Detail

Tender Details

  • Company በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት
  • Address ማዘጋጃ ቤት 2ኛ ፎቅ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ክፍለ ከተማ አራዳ ወረዳ 1 ሚኒሊክ አደባባይ /ፒያሳ/ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ፊት ለፊት : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0118680464
  • Website
  • Deadline03 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • opening date2025-10-03 00:00:00
  • Categories Maintenance And Repair , Printing And Publishing , Electronics Materials

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት


ብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 001/2018

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የግዥና ንብ/አስ/ጠቅ/አገ/ዳይሬከቶሬት በ2018 በጀት ዓመት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

1 ሎት አንድ- የግማሽ ሊትር ውሃ ግዥ

2. ሎት ሁለት፡- የሕትመት አገልግሎት ግዥ

3. ሎት ሦስት፡ የኤሌክትሮኒከስ ዕቃዎች ጥገና አገልግሎት

4 ሎት አራት፡- የመኪና /የተሽከርካሪ) የጥገና አገልግሎት

መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው:-

1, በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባ የምስከር ወረቀት ያላቸው!

2.የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ/የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን ማቅረብ የሚችሉ፣

3.የአቅራቢነት ሰርተፊኬት ያላቸው፣ የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር/ Tin No / ያላቸው

4. ተጫራቾች የሚያሲዙት የጨረታ ማስከበሪያ/CPO

ሀ. ለሎት አንድ 2,000 ብር /ሁለት ሺህ ብር

ሊ ለሎት ሁለት 5,000 ብር/አምት ሺህ ብር/

ሒ ለሎት ሦስት 3,000 ብር/ሶስት ሺህ ብር/

መ. ለሎት አራት 10,000 ብር /አምስት ሺህ ብር

ተጫራቾች በባንክ የተረጋገጠ በመቤታችን ስም የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማቅረብ ነግር ግን ያላስያዘ ቢኖር ከጨረታ ውጪ ይሆናል፣

5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት የሚችሉት ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ይሆናል፡፡

6, ማንኛውም ተጫራቾች ከተራ ቁጥር 1 እስከ 4 የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ህጋዊ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ጀምሮ ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ፒያሳ/ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ-ክርስቲያን ፊት ለፊት በሚገኘው ማዘጋጃ ቤት የከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት 2ኛ ፎቅ ፋይናንስ ዳይሬከቶሬት ቢሮ የማይመለስ 200 ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፣

7 አሸናፊው ድርጅት ጥራቱን ያልጠበቀ ዕቃ ወይም አገልግሎት ካቀረበ በራሱ ወጪ የመለወጥ ግዴታአለበት፣

8. መ/ቤቱ ካቀረበው ሰነድ ውጪ በሌላ ሰነድ በአማራጭነት ማቅረብ አይቻልም፣ ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ቴከኒካልና ኦርጅናል እንዲሁም ፋይናንሽያልና ኦርጅናል ዋጋ ሞልታችሁ በተናጠል ለየብቻ በፖስታ አድርጋችሁ የድርጅታችሁን ማህተምና ፊርማ በማድረግ በግዥና ንብረት አስተዳደር ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬከቶሬት ቢሮ ቁጥር 342 ለጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባችሁ፣

9. ጥቃቅንና አነስተኛ ተጫራቾች ለምትጫረቱባቸው ዕቃዎች የጨረታ ሰንዱን በነፃ ለመውሰድ

ሀ. ካደራጃችሁ መ/ቤት ደብዳቤ ማምጣት አለባችሁ፤

ሊ ሰነዱን በነፃ ለመውሰድ በመመሪያ መሰረት ለምታቀርቡት ዕቃ አምራች መሆን አለባችሁ፣

10, ተጫራቾች መ/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ሳይኖርበት በትከከል መሙላት አለባቸው፤

11. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ አሸናፊው ድርጅት ባሸነፈበት ዕቃ ወይም አገልግሎት ላይ ውል ሲገባ የጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርበታል፣ እንዲሁም አሸናፊ የሆነው ድርጅት አሸናፊነቱ እንደተገለፀለት ጨረታ ተከፍቶ ውጤት ከተለጠፈ ከ8 የሥራ ቀናት በኋላ በመ/ቤታችን ቀርቦ ውል መግባት አለበት፣

12. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ጋዜጣው ከወጣበት በ11ኛው ተከታታይ የሥራ ቀናት 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ከኛ ቀን የበዓል ቀን ከሆነ ቀጣይ ባለው የሥራ ቀናት ውስጥ የሚከፈት ይሆናል፡፡

ማሳሰቢያ:-

1. ተጫራቾች የቀረበው ዋጋ ሻትን ያካተተ መሆኑንና ያላካተተ መሆኑን መግለጽ አለባችሁ ይህ ካልሆነ ግን መ/ቤቱ የቀረበውን ዋጋ ቫትን እንዳካተተ አድርጎ ይወስደዋል፡፡

2. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡- አዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ማዘጋጃ ቤት 2ኛ ፎቅ ከፍለ ከተማ አራዳ ወረዳነ ምኒልክ አደባባይ /ፒያሳ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ፊት ለፊት ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር0118680464 ይደውሉ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት

Save Tender