Tender Detail

Tender Details

  • Company ZEMEN CONSTRUCTION CORPORATION (ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን)
  • Address ባ/ዳር ከተማ ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ቀበሌ 11 (ባህር ዳርዩኒቨርሲቲ ጥበብ ህንጻ አካባቢ የቀድሞው የአማራ ከተሞች ልማት አ.ማ ግቢ ውስጥ) እና አዲስ አበባ ለገሀር አመልድ ኢትዮጵያ ህንጻ 7ኛ ፎቅ በሚገኘው ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ቢሮ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 058-218-0538
  • Websitehttps:// zcc.org.et
  • Deadline10 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • opening date2025-10-10 00:00:00
  • Categories Audit Service

የዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን የ2017 በጀት ዓመት ሂሣብን በተፈቀደላቸው ኦዲተሮች ኦዲት ለማስደረግ ይፈልጋል፡፡


የሂሳብ ምርመራ (የኦዲት) አገልግሎት

ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ሰነድ ቁጥር 03/2018

የዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን የ2017 በጀት ዓመት ሂሣብን በተፈቀደላቸው ኦዲተሮች ኦዲት ለማስደረግ ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም እያንዳንዱ ተጫራች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች በማሟላት በጨረታ ለመወዳደር ይችላል፡፡

1 የድርጅቱን ሂሳብ በIFRS መሰረት ኦዲት ለማድረግ የሚያስችል የኦዲተርነት የሙያ ፈቃድ፤ የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር Tax identification Number (TIN) ያለው፤

2. የዘመኑን ግብር ከፍሎ የሙያ እና የንግድ ፈቃዱን ያሳደሰ፣

3. ተጫራቾች ወቅታዊ ብቃታቸውንና ሙያዊ ስነ ምግባራቸው በተመለከተ ከፈቃድ ሰጪዉ አካል ከዋናው አዲት መስሪያ ቤት እና ከኢትዪጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ፤ ወይም ከሂሳብ አዋቂዎችና የግል ኦዲተሮች ማህበር እንዲሁም ከዚህ በፊት ኦዲት ከአደረጋቸው የልማት ድርጅቶች የመልካም ስራ አፈጻጸም ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት ፣

4. የሂሣብ ምርመራው (ኦዲቱ) በባህርዳር ከተማ በሚገኘው የድርጅቱ ቅጥር ግቢ መሆኑን አውቆ

5. ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ15 የሥራ ቀናት ባ/ዳር በሚገኘው ኮርፖሬሽናችን ወይም አዲስ አበባ በሚገኘው የድርጅታችን ማስተባበሪያ ጽ/ቤት አመልድ ህንጻ ሰባተኛ ፎቅ ላይ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር ከፍሎ ከድርጅቱ በመግዛት መጫረት ይቻላል፡፡

6. ተጫራቾች ጠቅላላ ዋጋቸውን (ታክሱን ጨምሮ) በጨረታ መመሪያው መሰረት በመሙላት "የቴከኒከ ማወዳደሪያ ሰነድ” ፣ “የዋጋ ማወዳደሪያ ሰነድ” እና “የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /Bid Bond/ ማስያዣን በ2 የተለያዩ ፖስታዎች በማሸማ የጫረታ ማስከበሪያው ሰነድ የታሸገበትን ፖስታ የቴከኒካል መወዳደሪያው ሰነድ ካለበት ፖስታ ውስጥ አስገብቶ በማሸግ በተራ ቁጥር 5 በተገለጸው የስራ ቀናት ውስጥ ባህርዳር በሚገኘው የኮርፖሬሽኑ ቢሮ ቁጥር 107 ለዚሁ ጉዳይበተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ ኮላይ በተገለጸው መሰረት ሰነዶቹን አዘጋጅቶና አሽጎ ያልቀረበ ተወዳዳሪ ወይም ተጫራች ከውድድር ውጭ ይሆናል::

7. የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከቀኑ በ8.00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከቀኑ በ8.30 ሰዓት በኮርፖሬሽኑ ቢሮ 1ኛ ፎቅ ግዥ ከፍል ቢሮ ቁጥር107 ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ባሉበት ጨረታው ይከፈታል፡፡15ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው ቀን 8፡30 ይከፈታል፡፡

8. ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

ስልክ ቁጥር 058-321-7806/0918292107/

የዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን

Save Tender