የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳዳር ኮርፖሬሽ በውስጡ የሚያስተዳድራቸው በኮርደርልማት የለሙ በእቃቂ ኮዬ፣ መገናኛ፣ ሽሮ ሜዳ አካባቢ፣ ግንፍሌ፣ ሳር ቤት፣ ለቡ፣ ጀሞ፣ መካኒሳ፣ ኦሮሚያ ኮንዶሚንየም፣ ቡልቡላ፣ ለሚኩራ ፣ ሰሚት፣ አቦ አካባቢ፣ እንጦጦ ፓርክ ውስጥ፣ ጎሮ፣ ኮሪያ ፓርክ ውስጥ፣ ልደታ፣ ገርጂ መብራት ሀይል አካባቢ፣ ገርጅ ኦቪድ ሪል ስቴት አካባቢ ቡልቡላ መንገድ፣ስብሰባ ማዕከል፣ ቀበና፣ በአራት ኪሎ ፕላዛ (Underpass) ውስጥ የሚገኙ ሱቆችን እና ቦታዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በኪራይ ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 12
የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን በስሩ ያሉትን ለተለያዩ ፓርኮች ማለትም
ሎት 1: - የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳዳር ኮርፖሬሽ በውስጡ የሚያስተዳድራቸው በኮርደርልማት የለሙ በእቃቂ ኮዬ፣ መገናኛ፣ ሽሮ ሜዳ አካባቢ፣ ግንፍሌ፣ ሳር ቤት፣ ለቡ፣ ጀሞ፣ መካኒሳ፣ ኦሮሚያ ኮንዶሚንየም፣ ቡልቡላ፣ ለሚኩራ ፣ ሰሚት፣ አቦ አካባቢ፣ እንጦጦ ፓርክ ውስጥ፣ ጎሮ፣ ኮሪያ ፓርክ ውስጥ፣ ልደታ፣ ገርጂ መብራት ሀይል አካባቢ፣ ገርጅ ኦቪድ ሪል ስቴት አካባቢ ቡልቡላ መንገድ፣ስብሰባ ማዕከል፣ ቀበና፣ በአራት ኪሎ ፕላዛ (Underpass) ውስጥ የሚገኙ ሱቆችን እና ቦታዎች ለማከራየት
ሎት 2 ፡- ገዳመ ኢየሱስ ፓርከን ሙሉ ለሙሉ ለሶስተኛ ወገን በማስተላለፍ እንዲተዳደርለማከራየት፣
ሎት 3 ኮልፌ ፓርክን ሙሉ ለሙሉ ለሶስተኛ ወገን በማስተላለፍ እንዲተዳደር ለማከራየት፣
ሎት 4 ፡ አምሳደር ፓርከን ሙሉ ለሙሉ ለሶስተኛ ወገን በማስተላለፍ እንዲተዳደር ለማከራየት፣
ሎት 5 ፡-ሚሊንየም ፓርክን ሙሉ ለሙሉ ለሶስተኛ ወገን በማስተላለፍ እንዲተዳደር ለማከራየት፣
ሎት 6: መለስ ፓርክን ሙሉ ለሙሉ ለሶስተኛ ወገን በማስተላለፍ እንዲተዳደር ለማከራየት፣
ሎት 7 ፡-አቃቂ ፓርከ ሙሉ ለሙሉ ለሶስተኛ ወገን በማስተላለፍ እንዲተዳደር ለማከራየት፣ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በኪራይ ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የተጠቀሱትን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች ተጋብዘዋል፡፡
1. ተጫራቾች በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ አለባቸው፡፡
2. ፓርኮቹ ውስጥ ገብቶ ለመስራት ፍቃደኛ የሆነና ከተቋማችን ጋር ውል ገብቶ በገበያ ጥናት እና የመነሻ ዋጋ መሰረት ተወዳድረው አስፈላጊውን ከፍያ የሚከፍልና በውሉ መሰረት ግዴታውን መወጣት የሚችል፡፡
3. በግቢ ያሉ ፋውንቴኖችንና ፣ መናፈሻዎችን ፣ የመጸዳጃ ቤቶችን ፣ የጽዳት ፣ የጥበቃ የተለያዩ ጥገናዎችን ከሌሎች ተከራዮች ጋር በመሆኑ ማስጠገን ፣ መቆጣጠርና በአግባቡ ማስተዳደርየሚችል፡፡
4. ለህዝብ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ተመጣጣኝ የገበያ ዋጋ ለማቅረብ ፍቃደኛ የሆነ፡፡
5. ኮርፖሬሽኑና የከተማ አስተዳደሩ በሚወጣው የስራ ሰአት ፣ ቅዳሜ እና እሁድ ፣ በአላትንእንዲሁም ምሽትን ጭምሮ አገልግሎት መስጠት የሚችል፡፡
6. አሸናፊነት ከታወቀ በኃላና ውል ከወሰደ በኃላ በ3 ቀን ውስጥ ስራ መጀመር የሚችል፡፡
7. ስታንዳርዱን የጠበቀ እና የኮሪ ደር ልማቱን የሚመጥን እቃዎችን ይዞ መግባት የሚችል፡፡
8. ከተቻለ በሬስቶራንት ፣ በካፌ እና ህዝብ መዝናኛ ፓርከ ላይ ልምድ ያለውና መረጃ ማቅረብ የሚችል።
9. ተጫራቾች ለእያንዳዳቸው ሎቶች 50,000.00 (ሀምሳ ሺ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲፒኦ ወይም ባንከ ጋራንቲ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደርኮርፖሬሽን ስም ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
10. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 500 /አምስት መቶ ብር/ መገናኛ ዘፍመሽ ፊት ለፊት ታሜጋዝ ህንጻ ላይ ሶስተኛ ፎቅ የፋይናንስ ዳይሬከትሬት ቢሮ ውስጥ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አስር ተከታታይ የስራ ቀን ከጠዋት 2፡30 እስከ 11.30 ሰዓት ድረስ በመቅረብ መግዛት ይቻላል፡፡
11. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ፋይናንሻል ዶከመንት እና ቴከኒካል ዶከመንት ለየብቻ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሳጥኑ እስከሚታሸግበት ከ10ኛው ተከታታይ የስራ ቀን በኃላ በአለው 11ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ድረስ ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
12. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ሳጥኑ ታሽጎ በዚያው ቀን ጠዋት 4፡30 መገናኛ ዘፍመሽ ፊት ለፊት ታሜጋዝ ህንጻ ላይ ሶስተኛ ፎቅ በግዥና ንብረት ዳይሬክትሬት ቢሮ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል፡፡
13. የጨረታ መክፈቻው ቀን ቅዳሜና እሁድ ላይ የሚውል ከሆነ በቀጣዩ ሰኞ በተጠቀሰው ሰዓት ተዘግቶ የሚከፈት ይሆናል፡፡
14. ዘግይቶ የደረሰ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
15.ኮርፖሬሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለተጨማሪ መረጃ፡-ስልክ ቁጥር 077619010 /0977246014 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች
አስተዳደር ኮርፖሬሽን
