Tender Detail

Tender Details


በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በኢሉባቦር ዞን የበቾ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዘመን ወረዳው በሥሩ ላሉት የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች እና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች አገልግሎት የሚውል የተለያዩ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል፡፡


2 ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በኢሉባቦር ዞን የበቾ ወረዳ ////ቤት 2018 በጀት ዘመን ወረዳው በሥሩ ላሉት የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች እና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች አገልግሎት የሚውል የተለያዩ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል፡፡

ተ.ቁ

የእቃው አይነት

1

የመንገድ ሥራ ማሽኖች ኪራይ

2

ሞተር ሳይክል

3

የግንባታ እቃዎች

በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶችን ማሟላት ይጠበቅባችኋል፡፡

1. ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን (2018) ዓመት ግብር መከፈላቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤

2. VAT እና TIN ተመዝጋቢ መሆናቸውን ማቅረብ የሚችሉ፤

3. በመንግሥት ግዢ ላይ እንዳይሳተፉ ያልታግዱ፤

4. ከዚህ በፊት በወረዳው ሠርተው ከሆነ ከወረዳው ጋር በመግባባት የሠሩ ወይም ተጣልተው ያልተካሰሱ እና ለመልካም ሥራ አፈጻጸም ከበቾ ወረዳ መንገድ እና ሎጀስቲከስ /ቤት የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

5. የጨረታ ማስከበሪያ ከተወዳደሩበት የጨረታው ዓይነት 50,000 ብር በባንክ በተመሰከረ ሲፒኦ ወይም በጥሬማስያዝ /በሕግ በተቀመጠ/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

6. ተጫራቾች ጨረታው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት የጨረታውን ሰነድ ከበቾ ወረዳ ////ቤት በብር 500 ከቢሮ ቁጥር 11መግዛት ይችላሉ፡፡

7. ተጫራቾች በዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱ ላይ ዋጋ የሰዓት፣ የቀን ወይም የቢያጆ ሲሞሉ በማያሻማ ጽሑፍና የድርጅቱ ማህተም፤ የኃላፈው ፈርማ በሁሉም ገጽ ላይ በጥንቃቄ ተደርጎ ይህን ሰነድና ለውድድር የሚያበቁ ማስረጃዎችን ኦሪጅናልና ፎቶ ኮፒ በተለያየ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

8. የጨረታው መክፈቻ ቀን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ 11ኛው የሥራ ቀን ሲሆን በቅደም ተከተል 3:00 ሰዓት ለጨረታው በተዘጋጀ ሣጥን የጨረታው ሰነድ ማስገቢያ ሰዓት ሲሆን 400 ሰዓት ተወዳዳሪዎች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም ካልተገኙም ጨረታው ይከፈታል፡፡

9. 11ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ይሆናል፡፡

10. ዋጋ ማቅረቢያ ላይ ስርዝ ድልዝ የሌለውና የብርና የሣንቲም አፃፃፍ አሻሚና የማይነበብ ከሆነ የተወዳዳሪው የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም::

 

11. አሸናፊ ተጫራቾች ለመልካም ሥራቸው አፈጻፀም ስምምነት እንዲሆን ያሸነፉበትን ጨረታ 10% በባንክ በተመሰከረ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ በማስያዝ /ቤሕግ በተቀመጠ/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

12. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸኑን እስከ በቾ ወረዳ ////ቤት እና ሥራ ቦታ /ላይት/ ማስገባትና ከአንዱ ቦታ /ላይት/ ወደ ሌላ ቦታ /ሳይት/ ሥራ የሚሠራበት ሳይት ማቅረብ /ማንቀሳቀስ/ የሚችሉ፡፡

13. የማሽኑ የማስጫኛ እና ማውረጃ በአሸናፊ ድርጅት የሚሸፈን ይሆናል፡፡

14. አሸናፊ ተጫራቶች የስምምነት ውል ጨረታውን በአሸነፉ 5 ተከታታይ የሥራ ቀን መፈፀም ይኖርባቸዋል፡፡

15. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸኑን በፈጸሙት ስምምነት መሠረት ካላቀረቡ ለሥራቸው አፈጻፀም ያስያዙት 10% ለመንግሥት ገቢ ይሆናል፡፡

16. ከላይ የተዘረዘሩት ማሽኖች እንደአስፈላጊነቱ ለሥራ በሚፈለግበት ሰዓት ማሽኑን ሳይት ማስገባት የሚችሉ፡፡

17. ተጫራቾች ካቀረቡት የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ የተሻለ ዋጋ /List bidder/ የማሸኑ አጠቃላይ ድምር ባቀረበው ዋጋ እሸናፊ ይሆናል፡፡

18. ተጫራቾች መብትና ግዴታውን አውቀው መወጣት የሚችሉ መሆን አለበት፡፡

19. /ቤቱ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

20. ይህ ሰነድ የጨረታው አካል ነው፡፡

21. ለበለጠ መረጃ በሞባይል ቁጥር፡- 09-25-05-56-55/ 09-52-35-95-60/ 09-11-27-81-55

የተወዳዳሪው ድርጅት ማህተም የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ (ተወካይ) ስምና ፊርማ መሆን አለበት፡፡

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በኢሉባቦር ዞን የበቾ ወረዳ ////ቤት

Save Tender