የሰመራ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተለገጹ የተወረሱ ዕቃዎችን በግልጽ እና በሐራጅ ጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ ጨ.ቁ 03/2018 ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የሰመራ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተለገጹ የተወረሱ ዕቃዎችን በግልጽ እና በሐራጅ ጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ ጨ.ቁ 03/2018 ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
ዘርፍ |
የጨረታው ዓይነት |
እቃው ያለበት ቦታ |
|
1 |
ጫማዎች |
ሐራጅ ጨረታ |
በሰመራ /ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ ውርስ ዕቃ መጋዘን |
|
2 |
ልዩ ልዩ ዕቃዎች |
ሐራጅ ጨረታ |
በሰመራ ጉቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ ውርስ ዕቃ መጋዘን |
|
3 |
ፕላስቲክስ ሸራ ዕቃዎች |
ግልጽ ጨረታ |
በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ ውርስ ዕቃ መጋዘን |
|
4 |
አልባሳት |
ግልጽ ጨረታ |
በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ ውርስ ዕቃ መጋዘን |
|
5 |
ምግብ ነክ ዕቃዎች |
ግልጽ ጨረታ |
በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ ውርስ ዕቃ መጋዘን |
|
6 |
ኮስሞቲክስ ዕቃዎች |
ግልጽ ጨረታ |
በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ ውርስ ዕቃ መጋዘን |
|
7 |
መብራትና የመብራት ተጓዳኝ ዕቃዎች |
ግልጽ ጨረታ |
በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ ውርስ ዕቃ መጋዘን |
|
8 |
የመኪና መስታወት ዕቃዎች |
ግልጽ ጨረታ |
በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ደረቅ ወደብ ውርስ ዕቃ መጋዘን |
በመሆኑም ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጫረት የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡-
- በጨረታው ሽያጭ ስርዓት ለመወዳደር የሚፈልግ ተጫራች በዘርፉ የጸና የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ የግብር ከፋይመለያ ቁጥር እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ (ጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ ክሊራንስ) ማቅረብ ያለበት ሲሆን የሚወዳደሩበት የጨረታ ዓይነት መነሻ መሸጫ ዋጋው ከብር 500 ሺ በታች የሆነ ማንኛውም እቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት ማስረጃ ማቅረብ አያስፈልገውም፡፡ በግልጽ ጨረታ ለሚወዳደሩባቸው እቃዎች ከላይ የተጠየቁትን መረጃዎች ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኤንቨሎፕ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ያለበት ሲሆን ለሐራጅ ጨረታ ከላይ የተጠየቁትን መረጃዎች በጨረታ መክፈቻው ቀንና ሰዓት ማቅረብ ይኖርበታል፤
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ ጠዋት ከ1፡00-5፡00 ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በመገኘት ይህ ጨረታ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ሰመራ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ውርስ መጋዘን አስተዳደር የስራ ሂደት 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 30 በመምጣት መግዛት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) እና በሐራጅ ጨረታ ለሚወዳደሩባቸው ጫማዎች ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺ ብር) እና ለልዩ ልዩ ዕቃዎች ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺ ብር) ለጨረታ ዋስትና ዋስትና (CPO) በቅ/ጽ/ቤቱ ስም ETHIOPIAN CUSTOMS COMMISSION SEMERA BRANCH OFFICE በሚል በባንክ አሰርተው ማስያዝ የሚጠበቅባቸው ሲሆን ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሰመራ እና ከሎጊያ ቅርንጫፎች ብቻ መዘጋጀት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ የጊዜ ሰሌዳ (ስኬጁል) መሠረት መጫረት ይችላሉ፡፡
|
ተ.ቁ |
የቅ/ጽ/ቤቱ ስም |
የጨረታው አይነት |
የንብረት መመልከቻ ቀን የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ |
የጨረታው መዝጊያ እና መክፈቻ ቀንና ሰዓት |
|
1 |
ሰመራ ጉ/ቅ/ፅ/ቤት |
ግልጽ ጨረታ |
እስከ 27/01/2018 |
28/01/2018 ዓ/ም 3፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን 3፡45 ሰዓት ይከፈታል |
|
2 |
ሰመራ ጉ/ቅ/ፅ/ቤት |
በሐራጅ ጨረታ |
እስከ 27/01/2018 |
28/01/2018 ዓ/ም 4፡00 ሰዓት ይከፈታል |
- የጨረታው መክፈቻ ቦታ ፡- በሰመራ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ያስያዙትን ዋስትና (CPO) በተመለከተ ለአሸናፊው ተጫራች ካሸነፉት የዕቃ ዋጋ ላይ የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች የጨረታ ውጤቱ በተገለጸ በ3 (ሶስት) ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ5 (በአምስት) ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን እቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ እቃውን መረከብ ያለበት ሲሆን ይህን ባይፈጽም ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ዋስትና ለመስሪያ ቤቱ ገቢ ተደርጎ ዕቃው በድጋሜ ለጨረታ የሚቀርብ ሲሆን ነገር ግን የእቃውን ዋጋ ገቢ አድርጎ በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ እቃውን ያላነሳ እንደሆነ ለሚቆይበት ተጨማሪ ጊዜ የመጋዘን ኪራይ የሚከፍል ይሆናል፡፡ ሆኖም እቃውን በሁለት ወር ውስጥ ካላወጣ ለንብረቱ የተከፈለው ዋጋ ለመስሪያ ቤቱ ገቢ ሆኖ እቃው እንደተተወ ተቆጥሮ በሽያጭ ይወገዳል፡፡
- ቅ/ጽ/ቤቱ ለጨረታ የቀረበውን እቃ ብዛት ለመጨመርም ሆነ ለመቀነስ ሙሉ መብት አለው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ መረጃ በስ/ቁ:- 0333662302/0333665004 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
ሰመራ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
