በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የስልጤ ዞን የወራቤ ከተማ አስተደዳር ፋይናንስ ጽ/ቤት ለሴክተር መሥሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውል ሞተር ሳይክል በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የስልጤ ዞን የወራቤ ከተማ አስተደዳር ፋይናንስ ጽ/ቤት ለሴክተር መሥሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውል ሞተር ሳይክል በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም፡-
- በመስኩ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፤
- የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፤
- በመንግሥት ግዢ ለመሳተፍ የአቅራቢነት ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፤
- የጨረታ ዋስትና 50,000 በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ የሚችሉ፤
ተጫራቾች ሰነዱን ከወራቤ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት በመምጣት የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 300 /ሶስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል መግዛት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን፤ የጨረታ ሰነዱን አንድ ኦሪጅናልና ሁለት ፎቶ ኮፒ ለየብቻ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት በኋላ ባለው የሥራ ቀን በ4፡00 ሰዓት ድረስ በጽ/ቤቱ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ሳጥኑ በዚሁ ዕለት በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በ4፡30 ሰዓት መገኘት በሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
ማሳሰቢያ፡-
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የተሞላው ዋጋ መግለጫ ካልተሰጠበት ከነቫት ተደርጎ ይወሰዳል
ለበለጠ መረጃ፡- 046-7-71-02-11
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የስልጤ ዞን የወራቤ ከተማ አስተደዳር ፋይናንስ ጽ/ቤት
