በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን ስር ላለው የሠራተኞች መዝናኛ ክበብ ለመስተንግዶ አገልግሎት ላይ የሚውሉ እቃዎች፣ ለሰውነት ስፖርት እንቅስቃሴ የሚሆኑ ማሽኖች፣ እንዲሁም በተቋሙ ስር ለሚገኙ የሥራ ክፍሎች ለተለያዩ ስራዎች አገልግሎት ላይ የሚውሉ ዕቃዎችን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች በጨረታ እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡- አ/አ/ስ/ም/ጸ/ሙ/ኮ/02/2018
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን ስር ላለው የሠራተኞች መዝናኛ ክበብ ለመስተንግዶ አገልግሎት ላይ የሚውሉ እቃዎች፣ ለሰውነት ስፖርት እንቅስቃሴ የሚሆኑ ማሽኖች፣ እንዲሁም በተቋሙ ስር ለሚገኙ የሥራ ክፍሎች ለተለያዩ ስራዎች አገልግሎት ላይ የሚውሉ፡-
- ሎት 1 - ጀነሬተር ለሰውነት ስፖርት እንቅስቃሴ የሚሆኑ ማሽኖች፣
- ሎት 2 - የሠራተኞች መዝናኛ ክበብ ለመስተንግዶ አገልግሎት ላይ የሚውሉ ልዩ ልዩ እቃዎች፤
- ሎት 3 - የፈርኒቸር እቃዎች፣ የብፌ ጠረጴዛ፣ የካፌ መመገቢያ ጠረጴዛ እና ኮፊ ቴብል፤
- ሎት 4 - የተሽከርካሪ ኪራይ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች በጨረታ እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
- አግባብነት ያለው የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ እንዲሁም በእቃ አቅራቢነት ዝርዝር ለመመዝገባቸው ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸው እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፣
- ታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፤
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር ለሎት 1 ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር)፣ ለሎት 2 ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር)፣ ለሎት 3 ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር)፤ ለሎት 4 ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ/ CPO ብቻ ማቅረብ የሚችሉ፤
- ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ ተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ11 ተከታታይ ቀናት የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር ለእያንዳንዱ ሎት ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በአ/አ/ስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን አካውንት ቁጥር 1000540125183 በመክፈል የተከፈለበትን ደረሰኝ በመያዝ የጨረታ ሰነዱን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን በፋይናንስ ዳይሬክቶሬት/ ፒያሳ ኤሌያና ሆቴል ፊት ለፊት በሚገኘው ትንሳኤ ሕንጻ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 502 በመገኘት መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 11 /አስራ እንድ/ የስራ ቀናት በአየር ላይ ከዋለ በኋላ በ11ኛው የሥራ ቀን በ4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ የሥራ ቀን በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት አበባ ከተማ አስተዳደር ስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን በግዥ ንብረት አስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 502
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዳቸውን በጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለጸው መሰረት ሞልተው እና ማህተም በማድረግ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቶች ዶክመንታቸውን (ቴክኒካልና ፋይናንሽያል) ዋናውንና ኮፒውን ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዋጋ በተነገራቸው ቀን ቀርበው ውላቸውን በመፈረም ውል ማስከበሪያ 10% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ቫትን አካተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱባቸውን የካፍቴሪያ እቃዎች ለመለየት የሚያስችል ሣምፕል ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ለቡና ማሽን፣ ሲሊንደርና ሌሎች እቃዎች በተጠየቀው ስፔስፊኬሽን መሰረት ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው።
- ለተጠየቁት የፈርኒቸር እቃዎች ተያይዞ በቀረበው ስፔክ መሰረት መቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱባቸውን ጀነሬተር እና የሰውነት ስፖርት እንቅስቃሴ የሚሆኑ ማሽኖች እቃዎች ለመለየት በቀረበው ስፔስፊኬሽን መሰረት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዞ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
- አንድ ተጫራች ሌላው በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ውል ከፈረመበት ቀን አንስቶ በ15 ቀን ውስጥ እቃውን ያቀርባል፡፡
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ ወይም ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
- ተጫራቾች የተጠቀሱትን እቃዎች በሙሉ ወይም በከፊል መጫረት ይችላሉ፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በግዥ ንብረት አስተዳደር እና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 502 በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 011-1-26-66-76/ 09-25-98-42-12/ 09-11-68-70-90 ደውለው ያነጋግሩ፡፡ -
አድራሻ፡- አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ኤሊያና ሆቴል ፊት ለፊት ትንሳኤ ሕንፃ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስነ ምግባር ጸረ ሙስና ኮሚሽን የግዥ ንብረት አስተዳደር እና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት
